የፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በማዘመን ውብ ፣ ፅዱና ምቹ ከተማ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተባባሪ አቶ ሙሴ ገ/ስላሴ እንዳሉት 26 የህዝብ እና 14 የጋራ ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ መፀዳጃና ገላ መታጠቢያ ቤቶች እንደተገነቡ ገልፀው በተደራጁ ማህበራት አማካኝነት የገቢ መሰብሰብና የቁጥጥሩ ስራው በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡