18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በድምቀት ተከበረ።

18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በድምቀት ተከበረ። ጥቅምት 03/2018 (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 18ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ህዳሴ” በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡ የዘንድሮው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተለየ መልኩ በኢትዮጵያ የማንሰራት ዘመን ከፍታችንን የምናሳይበትና የይቻላል መንፈስን ያስመሰከርንበት ዓመት በመሆኑ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለየት ባለ መልኩ ተከብሯል፡፡ በሀገራችን ሰንደቅ ዓላማን ወጥ በሆነ መልኩ በሀገር ደረጃ ጥቅምት ወር በመጃመሪያው ሰኞ በሁሉም የመንግስት ተቋማት፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በተወካዮች ምክር ቤት፣ በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮችና በሁሉም ክልሎች በአንድ ቀንና በተመሣሣይ ሰዓት ተከብሯል፡፡

Share this Post