ቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ /BaSRINET/ ፕሮጀክት የአዋሽ ቤዚን ፕሮጀክት ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ።

ቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ /BaSRINET/ ፕሮጀክት የአዋሽ ቤዚን ፕሮጀክት ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀግብር ተካሄደ ።   አፋር#ሰመራ:ጥቅምት 04/2018 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ /BaSRINET/ ፕሮጀክት የአዋሽ ቤዚን ፕሮጀክት በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ለመግባት ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀግብር አካህዷል።   በማስጀመሪያ መርሀግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጉት የሚመሰረተው በውሃ ሀብት ላይ ነው ብለዋል ።   ክቡር ሚነኒስትሩ በኢትዮጵያ የተፋሰስ ስራ የተጀመረው በአዋሽ ተፋሰስ ላይ እንደነበረና ተፋሰሱ ከዚህ በፊት በጎርፍ ምክንያት የዜጎች የመፈናቀልና የችግር መንስኤ ሆኖ መቆየቱን አውስተው አሁን ግን በፕሮጀክቱ በተሰሩ ስራዎች ለአካባቢው ህብረተሰብ እፎይታና የኢኮኖሚ ምንጭ መሆን ችሏል ብለዋል።   ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ሲገባ ዘመናዊ የውሃ ሀብት መረጃ በተደራጀ ሁኔታ ስለምናገኝ ቀጣይ ስራችንን በተቀላጠፈና የበለጠ ውጤታማ በሚያደርግ መልኩ ለማከናወን ያግዛል ብለዋል። በፕሮጀክቱ ትግበራ በታቀደውና ከዚም በላይ ውጤት ለማምጣት ከከፍተኛ አመራር እስከ ባለሙያና ማህበረሰብ ድረስ በመናበብ ፣በመቀናጀትና በመተባበር መስራትና መትጋት አለብን ብለዋል ።   የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና በየክልሉ የልማትና ፕላን ቢሮ ሀላፊ የአዋሽ ቤዚን ባዜርኔት/BaSRINET/ ፕሮጀክት አርብቶ አደር ማህበረሰቡን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ እንደክልል ለፕሮጀክቱ ልዩ ቦታ አለን ብለው ለተግባራዊነቱም እጅ ለእጅ ተያይዘን በባለቤትነት ስሜት እንተጋለን ብለዋል ።   በመርሃግብሩ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና የዘርፉ አመራሮች ስለፕሮጀክቱ የእስካሁን ሂደት፣የትግበራ ምዕራፍና ተጠባቂ ውጤቶች ምን እንደሚመስሉ አጭርና ግልጽ ጽሑፍ አቅርበው በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ምላሽ፣ ማብራሪያና የወደፊት የትግበራ አቅጣጫም ተሰጥቷል።   በዕለቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣የአፋር ክልል ም/ር/ መስተዳድር፣ የክልሉ የፕላንና ልማትና ቢሮ ሀላፊ፣የክልሉ የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ፣የሚኒስቴሩ የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

Share this Post