በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቻችን ጉዳይ ኢትዮጵያ ያላት ጽኑና የማይቀር አቋም የቀጠናውን ተገቢ፣ ሚዛናዊና ፍትሀዊ የውሃ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው ተባለ።

በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቻችን ጉዳይ ኢትዮጵያ ያላት ጽኑና የማይቀር አቋም የቀጠናውን ተገቢ፣ሚዛናዊና ፍትሀዊ የውሃ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው ተባለ። ጥቅምት 21/2018 ዓ/ም ውኢሚ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአዲስ አባባ ሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት በኢትዮጽያ ውሃና ኢነርጂ ሀብት ማልማትና ማስተዳደር ዙሪያ በተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ የዘርፉን ጉዞ አቅጣጫ በሚያመላክት መልኩ በታላላቅ የሚሁራን ጽሑፎችና በፓናል ውይይቶች ግንዛቤ እያስጨበጠ ዛሬ አምስተኛና ማጠቃለያ ቀን ደርሷል። በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቻችን ጉዳይ ኢትዮጵያ ያላት ጽኑና የማይቀር አቋም የቀጠናውን ተገቢ፣ሚዛናዊና ፍትሀዊ የውሃ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የጎርፍ አዳጋ እንዳያጋጥም መከላከልና ለአየር ንብረት ለውጥ ተጽኖ የማይበገር አካባቢ የመፍጠር ዕድል እንጂ ለተፋሰሱ ሀገራት ውሃ ያጎደለ አልነበረም ያሉት ሚኒስትሩ ይህም ውሃን በፍትሃዊነትና በተገቢነት የመጠቀም አቋማችንን የሚገልጽ ነው ብለዋል ። ክቡር ሚኒስትሩ አክለው በነበረው በአራት ቀናት ቆይታም ይሁን በዕለቱ የሚቀርቡ ጽሑፎች፣ፓናል ውይይቶችና አውደ ርዕዮች ዋናው ጉዳይ ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በመለዋወጥ በትብብርና በቅንጅት በመስራት የማደግ ጽኑ ፍላጎትን መግለጫ ነው ብለዋል። የዘርፉን ጉዳይ ይዘው በዓለም ሀገራት በተለያዩ ትልልቅ መድረኮች ኢትዮጵያን በመወከል ተገኝተው ድል እየተቀዳጁ ያሉትን ጀግኖች ተደራዳሪዎችን ፣ድፕሎማቶችንና የዘርፉን ምሁራን አድንቀው ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

Share this Post