ክቡር ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ አምባሳደር አል-ዘይን ኢብራሂምን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ክቡር ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ አምባሳደር አል-ዘይን ኢብራሂምን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ህዳር 09/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር እና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ አምባሳደር አል-ዘይን ኢብራሂምን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።   ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ በውይይታቸው ኢትዮጵያና ሱዳን የቆየ የሁለትዮሽ የግንኙነት ታሪክ እንዳላቸው ገልፀው፤ በሱዳን መንግስት በኩል በኢነርጂው ዘርፍ ከኃይል አቅርቦት ጋር ስላለው ግንኙነት አብራርተዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ከሱዳን የኢነርጂ ሚኒስቴር ስለተላከው ደብዳቤ አመስግነው፤ ከኃይል አቅርቦት ጋር በተገናኘ የነበራቸውንም ግንኙነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡   አምባሳደር አል-ዘይን ኢብራሂምን ሁሴን በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን መልካም ግንኙነት ማጠናከር እንደሚፈልጉ ገልፀው፤ ቴክኒካል፣ ፖለቲካልና ስትራቴጂክ በሆኑ ጉዳዮች፣ ቅንጅታዊ አሰራር እና ወደፊትም በኃይል አቅርቦት ዘርፍ ላይ በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡   አምባሳደሩ ለተደረገላቸው አቀባበል በማመስገን፤ ከሱዳን የኢነርጂ ሚኒስቴር የተላከውን ደብዳቤ አስረክበው ዲጂታል ኤግዚቢሽንን ጎብኘተዋል፡፡

Share this Post