የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ላይ የጋራ ግንዛቤ ሊኖር ይገባል ተባለ።

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ላይ የጋራ ግንዛቤ ሊኖር ይገባል ተባለ። ህዳር 08/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ሰነድ የተቋሙን የአሰራር ስርዓት በማዘመን የተቋሙን ራዕይ ዕውን ለማድረግ የሚያስችል የዝግጅት ምዕራፍ ላይ የጋራ ግንዛቤ ሊኖር እንደሚገባ ተገለፀ።   መድረኩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በክቡር ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ ሪፎርሙን አስመልክተው ለተቋሙ ሰራተኞች ሰፊ ገለፃ እንደተሰጠ አስታውሰው፤ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም በተቋማችን እንዴት መተግበር እንዳለበት የምናይበት ሰነድ ነው ብለዋል።   በዚህ ሪፎርም ውስጥ ራሳችንን በመፈተሽ ብቃት ላይ ለመድረስ ሁሉም ሰራተኛ የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ሰነዱ ሁሉም ሰራተኛ በባለቤትነት ስሜት ተግባራዊ በማድረግ በስሙ ልክ ውሃና ኢነርጂን በሚገልፅ መልኩ የአሰራር ስርዓትን ለማዘመን በሚቀርበው ሰነድ ላይ በንቃት በመሳተፍ ሰነዱን የሚያዳብር አስተያየት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።   በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ አለሙ መንገሻ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም በስምንት አምድ ስር 15 ሰነዶችን በ25 ቀናት የተዘጋጁ ሲሆን በቀጣይ በዝግጅተ ምዕራፍ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችን፣ ስታንዳርዶችንና ማኑዋሎችን የማዘጋጀት፣ የህግ ማዕቀፎች የማሻሻልና የማዘጋጀት እንዲሁም የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የስትራቴጂክ ዕቅድ የመከለስ ስራ ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራትን እንደሚከናወኑም ገልፀዋል።   በዝግጅት ምዕራፍ በሚሰራው ሰነድ ላይ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት አቅርቦት ስርዓት መዘርጋት ላይ በትኩረት በመስራት ወደ ድጅታል የአሰራር ስርዓትን መጠናከር እንዳለበትም አቶ አለሙ አክለዋል።   ከኮሚቴ አወቃቀር ጋር ተያይዞ የሰው ኃይል በማደራጀት 5 አባላትን የያዘ አብይ ኮሚቴ፣ 31 አባላትን የያዘ 4 የቴክኒክ ኮሚቴ እና 150 አባላትን የያዘ ንዑሳን ኮሚቴዎች በማዋቀር ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በተውጣጡ ባለሞያዎች የ1 ቀን ገለፃና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አግኝተው፤ ሰነዶችን የማዘጋጀት ስራ እንደተሰራ እና ሪፎርሙን እስከ ታችኛው እርከን ለማድረስ የተግባቦት ሰነድ እንደሚዘጋጅም ተገልጿል።   በየአምዱ በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን እንደተቋም የሰው ኃይሉን በማደራጀት ከ85 በመቶ በላይ ውጤት ለማምጣትና የዝግጅት ምዕራፍ ደረጃን አጠናቀን ወደ ትግበራ ምዕራፍ ለመሻገር አመራሩ ከባለሞያዎች ጋር በጋራ በመሆን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውንም በውይይቱ ላይ ገልፀዋል።

Share this Post