የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የፕሮጀክት ግንባታ ለማከናወን ተስማማ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የፕሮጀክት ግንባታ ለማከናወን ተስማማ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የድሬዳዋ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ግንባታ ለማከናወን ስምምነት አድርጓል፡፡ ሚኒስቴሩ ስምምነት ያደረገው ከዮት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር ነው፡፡ በዚሁ ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትቴር ሚንስተር ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ፤ የድሬዳዋን ህዝብ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ዮት ኮንስትራክሽን በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ስራውን አጠናቅቆ እንዲያስረክብ አሳስበዋል፡፡ ፕሮጀክቱ መንግስት ከተሞችን ንፁህና ለእይታ ማራኪ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ጋር የተቆራኘ ነው ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በአካባቢው ለሚገኙ ሴቶችና ወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም አስረድተዋል፡፡ የዮት ኮንስትራክሽን ዋና ስራ ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሃንስ ሙሉጌታ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ለሀገር ያለውን ፋይዳ ከግምት በማስገባት በጥራትና በወቅቱ ለማጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆነን እንሰራለን ነው ያሉት፡፡ ግንባታና ጥገናው ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የሚከናወን ሲሆን በውሉ መሰረት በአንድ ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ገልጸዋል፡፡

Share this Post