በሶላር ሚኒግሪድ ዝርጋታ ፣ጥገናና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሰለጠኑ ሰልጣኞች የብቃት ምስክር ወረቀት ተሠጠ።
ህዳር 02/2018 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዩኤንዲፕ፣ ከአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲና ከአፍሪካ ሚኒ ግሪድ ፕሮግራም ጋረ በጋራ በመሆን በሶላር ሚኒግሪድ ዝርጋታ ፣ጥገናና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለ3 ወራት የአቅም ግንባታ ስልጠና የወሰዱ 50 ሰልጣኞች የብቃት የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።
መርሃግብሩን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዩኤንዲፒ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ይመስላል ተፈራ ኢትዮጵያ በሶላር ኢነርጂ የታደለች በመሆኗ ይህን ዕምቅ የሶላር ሀይል በበቂ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ሚኒስቴር የመስሪያ ቤቱ በዘርፉ የሚታየውን የብቃት ክፍተት በጥናት በመለየት ክፍተቱን ለመሙላት ስልጠናው ተዘጋጅቷል ብለዋል።
ዛሬ የምስክር ወረቀት የተቀበሉ ሰልጣኞች ትልቁ ተግባራቸው ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሶላርሚኒ ግሪዶችንዝርጋታ፣ጥገናና አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን ነው ያሉት አቶ ይመስላል ህብረተሰቡን ከማገልገል ባለፈ በሰለጠኑበት ሙያና ክህሎት የግል ገቢየቸውንም ለማሳደግ እንደሚያግዛቸው አብራርተዋል ።
በዩኤንዲፒ የታዳሽ ሀይል ስፔሻሊስት አቶ ዳርጌ አድነው የአፍሪካ የሚኒግሪድ ፕሮግራም በአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ21 ሀገራት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው እንደሀገር በዘርፉ የሚታየውን የአቅም ክፍተት የሚሞላ በመሆኑ ስልጠናው እጅግ ጠቃሚና ውጤታማ እንደሚሆን አምናለሁ ብለዋል።
በአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ የስታር ሴንተር/star -center/አስተባባሪ ዶ/ር ፍሬህይወት ወልደሐና ሰልጣኞችና አሰልጣኞች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ላሳዩት ትጋትና አፈፃፀም አመስግነው ሰልጣኞች ስልጠናውን ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ማሳየት አለባችሁ ብለዋል።
የዕለቱን መርሃ ግብር ሲመራ፣ሲያስተባብርና ሲያቀናጅ የነበረው በአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና የታዳሽ ሀይል ማዕከል ሀላፊ ዶ/ር ፍፁም ሳለሁ በስልጠና ወቅት ሰልጣኞችና አሰልጣኞ ስላሳዩት ትጋትና ጽናት አድንቀው፣ ሰልጣኞች ስለሰጡት ገንቢ አስተያየት አመስግነው ለቀጣይ ስራ ግብዓት እንደሚሆን ከገለፁ በኋላ ለተግባራዊነቱ ብዙ እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል ።
ሰልጣኝ ነፃነት ታዬ እና ሰልጣኝ ኢዩ ብርሃኑ በበኩላቸው በዘርፉ ስራ ላይ የቆዩ መሆናቸውን ገልፀው እስካሁን ካገኙት ስልጠናዎች የተለየና ጠቃሚ መሆኑን ገልፀው ውጤታማ ወደሚያደሚያደርጋቸው ስራ ለመሰማራት መንገዱ እንዲመቻችላቸውና ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ቀጣይ ስልጠናዎች ኦንላይን/online /ቢሆን ጥሩ እንደሚሆን ተናግረዋል ።