በዩኤንዲፒ ፕሮጀክት ለተመረጡ ባንኮችና ማይክሮፋይናንስ ተቋማት ስልጠና እየተሰጠ ነው
ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም (ው..ኢ.ሚ)በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዩኤንዲፒ ፕሮጀክት በቁጥር አስራ አምስት ለሚሆኑ ለተመረጡ ባንኮችና ማይክሮፋይናንስ ተቋማት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ አስመልክቶ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዩኤንዲፒ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ይመስላል ተፈራ እንደገለጹት የግልና የመንግስት ባንኮችና ማይክሮፋይናንስ ተቋማት በሚኒግሪድ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥና በፕሮጀክቱ በሚሰሩ የሶላር ሚኒግሪድ ትግበራዎች ለግል አልሚዎች የብድር አቅርቦት በማመቻቸት ትብብር እንዲያደርጉ ነው ብለዋል፡፡
በተለይም ኤሌክትሪክ በማይደርስባቸው አካባቢዎች ለሚተከሉ የሶላር ኢነርጂ አቅርቦቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የግሉ ዘርፍ ከመንግስት ጎን በመሆን ለሚያደርገው ድጋፍ ስልጠናው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋልም ተብሏል፡፡
ስልጠናው ለአንድ ቀን የሚካሄድ ሲሆን ቀደም ሲልም በተመሳሳይ መልኩ ለባንኮች የተሰጠ መሆኑን አቶ ይመስላል አስታውሰዋል፡፡