በከርሰ ምድር የውሃ ጥራት ክትትል ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በከርሰ ምድር የውሃ ጥራት ክትትል ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በባዘር ኔት እህት ፕሮጀክት በጣሊያን መንግስት የሚደገፈውና በዋቢ ሸበሌ፣ አዋሽ እና በደናክል ሃይድሮግራፊክ ተፋሰሶች የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር (IWRM) መሻሻልን የሚደግፈው ፕሮጀክት በከርሰ ምድር የውሃ ጥራት ክትትል ላይ ስልጠና እየተሰጠ ነው። መስከረም28/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በስልጠናው መክፈቻ የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአዋሽ ባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዮሀንስ ዘሪሁን በጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ በጋራ የተዘጋጀውና የከርሰ ምድር ውሃ ጥራትና ክትትል ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበረ ያለውን የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ለማስፈን ከባዘር ኔት ፕሮጀክት ጋር በጋራ የሚደግፍ በመሆኑ በተለይ የከርሰ ምድር ውሃ ጥራትና ክትትል በማድረግ በማበልጸግና በማቀብ በአርብቶ አደር አካባቢዎች ለመጠጥ፣ ለእንስሳት እና ለመስኖ አገልግሎት እንዲውል የተለያዩ ድጋፎችን ስለሚያደርግልን AICS እና የአውሮፓ ህብረትን በባዘርኔት ፕሮጄክት ስም አመስግነዋል። ከክልል እና ከቤዚን ጽ/ቤቶች የተውጣጡ ባለሙያዎች ስልጠናው በቲወሪና በተግባር የሚሰጥ በመሆኑ በንቃት እንዲሳተፉ እና ያገኙትን እውቀት ወደ ተቋሞቻቸው በመውሰድ መተግበር ይጠበቅባቸዋል በማለትም አቶ ዮሀንስ አሳስበዋል፡፡ ለዋቢ ሸበሌ፣ ለአዋሽ እና ለደናክል ሃይድሮግራፊክ ተፋሰሶች የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር (IWRM) መሻሻል አስተዋጽኦ (EU IWRM PROJECT ) ማናጀር ማርኮ ላንዲ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደርን ማሻሻል ለዋቢ ሸበሌ፣ አዋሽ እና ደናኪል ሃይድሮግራፊክ ተፋሰሶች የአካባቢን ዘላቂነት ማህበራዊ ፍትሃዊነት እና ኢኮኖሚያዊ አዋጭነትን ያገናዘበ ዘርፈ-ብዙ አካሄድን ያካትታል ብለዋል። ፕሮጀክቱ በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ምንጭ በጣሊያን መንግስት የሚተገበር መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡ የጣሊያን ትብብር ኤጀንሲ ፕሮጀክት ተወካይ እና የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ባለሙያ የሆኑት ሲሳይ ተክሉ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱ የባዘርኔት ፕሮጀክትን ለመደገፍ ታሳቢ ያደረገ እህት ፕሮጀክት መሆኑን ጠቅሰው በውሃ ጥራት፣ ቁጥጥር ፣ በከርሰ ምድር ውሃ ኬሚካላዊ እና የማይክሮባዮሎጂ ጥራት መሳሪያዎች፣ ቴክኒኮች እና ፕሮቶኮሎች ላይ ለባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው ስልጠናው የተግባር ልምምድን ያካተተ በመሆኑ ወደ መስክ ተወርዶ እንደሚሰጥም ገልጸዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋናነት ሚኒስትሪውን፣ የቤዚን ጽ/ቤቶችን እና ክልሎችን በገጸ ምድርና ከርሰ ምድር የውሃ ጥራት በአቅም ግንባታ እና በውሃ ጥራት መለኪያ መደገፍ፣በተፋሰስ መረጃ ስርአትና ሀይድሮሎጂ ዘርፍ መደገፍ እና ወደ ስራ ለማስገባት ሰርቶ ማሳያ በመስራት የተቀናጀ የውሀ ሀብት አስተዳርን በአርብቶ አደሩ አካባቢዎች ላይ መተግበር እንዲቻል ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ከጣሊያን በመጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና በበይነ መረብ እየተሰጠ ሲሆን በቀጣይ ሳምንትም የተግባር ስልጠና በአዋሽ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share this Post