በፈረንሳይ የአማካሪ ልማት ድርጅት በተጠናው የከተሞች ቅድመ መለያ መስፈርት እና የአዋጭነት የጥናት ሰነድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

በፈረንሳይ የአማካሪ ልማት ድርጅት በተጠናው የከተሞች ቅድመ መለያ መስፈርት እና የአዋጭነት የጥናት ሰነድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ልማት ፈንድ በፈረንሳይ የአማካሪ ልማት ድርጅት በተጠናው የከተሞች ቅድመ መለያ መስፈርት እና የአዋጭነት የጥናት ሰነድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡ ህዳር05/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የውሃ ልማት ፈንድ ከተቋቋመ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በተለይ በውሃ ፕሮጀክቶችና ሀብት በማሰባሳብ ውጤታማ ስራ መስራቱን ገልጸዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ በማከል የውሃ ልማት ፈንድ ከተቋቋመበት አላማ በፖሊሲ ከተቀመጠው የከተሞች ኢኮኖሚማና ማህበራዊ ሀብት ውስጥ አንዱ እና ሰብአዊ መብትም ጭምር በሆነው ንጽህናው የተጠበቀ ውሃ ለህብረተሰቡ ማድረስ ሲሆን በዚህ ደግሞ በከተሞች አካባቢ ብርድ በመስጠት እንዲተገብሩት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ለዚህም ይረዳው ዘንድ አማካሪ በመቅጠር የከተሞች ቅድመ መለያ መስፈርት እና የአዋጭነት የጥናት ሰነድ አስጠንቶ ለውይይት ማቅረቡን በመግለጽ ተሳታፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት በሰነዶቹ ላይ በትኩረት በመወያየት ሀሳብና አስተያየት በመስጠት ለሰነዱ ተጨማሪ ግብዓት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡ በተያያዘም የውሃ ልማት ፈንድ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዶጊሶ ጎና በበኩላቸው ተቋሙ ከተቋቋመ ከ23ዓመት በላይ መሆኑን አውስተው በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን መስፈርቱን ለሚያሟሉ ከተሞች ብድር ሲያበድር የቆየና አሁንም ይህን ስራ አጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አቶ ዶጊሶ በማከል እስካሁን ባለው ሂደትም ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ከልማት አካሎች 23.1 ቢሊየን ብር ሀብት አሰባስቦ ለ133 ከተሞችን ተጠቃሚ ያደረጉና በነዚህ ከተሞችም ከ8 ሚሊዮን በላይ ህብረተሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል፡፡ ስራውን በምንተገብርበት ወቅትም ከተሞች በረጂም ጊዜ አነስተኛ ወለድ ብድር ይሰጣቸዋል ስለሆነም ከተሞች የሚመዘኑበት መስፈርት የከተሞች ቅድመ መለያ አንዱ ሲሆን ሁለተኛው መስፈርቱን ያሟሉ ከተሞች ላይ አዋጭነት ጥናት ይካሄዳል በእነዚህ ሁለት ሰነዶች ለብድር መሰረት ሲሆኑ በፈረንሳይ የልማት ድርጂት አማካሪ ቀጥረው ለአንድ አመት ሲያስጠኑ መቆየታቸውን ገልጸው አሁን የጥናቱን ሰነድ የፌደራልና የክልል የውሃ ቢሮ ሃላፊዎች ከሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ለውይይት የቀረበና የሚጨመር ካለ በመጨመር የሚወጣም ካለ በማውጣት ለስትሬንግዝ ኮሚቴ ቀርቦ እንደሚጸድቅ ወደስራ እንደሚገባ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

Share this Post