በክቡር ሚኒስትሩ የሚመራው ሉካን ቡድን የመስክ ምልከታ አካል የሆነውን የሰመራ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ያለበት ሁኔታ ምልከታ አደረገ;;

በክቡር ሚኒስትሩ የሚመራው ሉካን ቡድን የመስክ ምልከታ አካል የሆነውን የሰመራ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት ያለበት ሁኔታ ምልከታ አደረገ።   የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ፣ የአፋር ክልል ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አህመድ ሻሚ የሠመራ ከተማ የመጠጥ ውሀ አገልግሎት ኃላፊ ና የኮንትራክተሩ ተወካይ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት የሰመራ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክትን ተመልክተዋል።   ከምልከታው በኋላ ፕሮጀክቱን እየገነባ ከሚገኘው ኮንትራክተር የክልሉ የውሀና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ በየደረጃ ካሉ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል።   በውይይቱ ላይ ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፕሮጀክቱ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲጠናቀቅ አሳስበዋል። አክለውም ክቡር ሚኒስቴሩ ስራውን ለማጠናቀቅ ለሚገጥም ተግዳሮቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም አረጋግጠዋል።   የአፋር ክልል ውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ በበኩላቸው፤ ስራው እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ክትትል እንደሚደርጉ ገልፀዋል። በቦታው የተገኘው የኮንትራክተር ተወካይ ስራውን ሌተ ቀን በመስራት በቀጣይ የተሻለ ደረጃ ማድረስ እንደሚቻል ቃል ገብተዋል።

Share this Post