በውሃ፣ በሳኒቴሽንና ኢነርጂ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ።
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀውና 2ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት አውደ ርዕይ እና ፓናል በተካሄደው 13ኛ ባለድርሻ አካል ፎረም ላይ
በውሃ፣ በሳኒቴሽንና ኢነርጂ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸ።
መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ሚካኤል መሀሪ 13ኛ ባለድርሻ አካል ፎረም በተለያዩ ምክኒያቶች በቀኑ መደረግ አለመቻሉን ገልጸው 2ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት አውደ ርዕይ ላይ መደረጉ የተሻለ ልምድ ለመውሰድ መልካም አጋጣሚን የፈጠረ ነው ብለዋል።
ዶክተር ሚካኤል በማያያዝ ባለፉት አመታት በፎረሙ ላይ በኢነርጂ፣ በውሀ፣ በሳኒቴሽን፣ በምግብ እና በአየር ንብረት የተሰሩ ስራዎች እና የተለያዩ ጥናቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግም ገልጸዋል።
በ13ኛ ባለድርሻ አካል ፎረም ላይም ባለፈው አመት እንደ ቤት ስራ በወሰድናቸው የመንግስትና አጋር አካላት የሚወስዱትን ድርሻ ማሻሻል፣ ከሀብት ማሰባሰብ እና ማስተባበር እንዲሁም ዘላቂነት ያለው የመጠጥ ውሃ መስኖ ላይ ሲጠቀሙበት የነበረውን የሀይል ምንጭ ጋር በተያያዘ ያለባቸውን ከፍተኛ ችግር በተለይ የነዳጀ ወጪን ከመሸፈን ጋር ተያይዞ የነበረውን ጥያቄ በሶላር መቀየር ላይ ጥሩ ስራ የተከናወነበት እንደነበር ገልጸዋል።
በተለይ እንደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ትልቅ አጀንዳ አድርጎ እየሰራ መሆኑን ከበቂ ማሳያ ጋር ለተሠብሳቢው ገልፅዋል።
በፎረሙ ላይ ከአለም በንክ፣ ከጣሊያን መንግስት፣ ከኔዘርላንድ ኤባሲ እና ከግል ሴክተሮች የመጡ ከፍተኛ ሀላፊዎች ንግግር ያደረጉና ጥናታዊ ጹሁፎች የቀረቡ እና ለቀጣይ ፎረም የቤት ስራን የወሰድንበት ነው በማለት አስተባባሪው አብራርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በ2ኛው የኢትዮጵያ ውሃና ኢነርጂ ሳምንት አውደ ርዕይ ላይ ፎረሙ መካሄድ መቻሉ ተሳታፊዎች እንደሀገር በውሃና ኢነርጂ ላይ ያመጣነውን ለውጥና ያለንበትን ደረጃ በተለይ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ ረገድ ያለንን ሚና ያሳየንበት ነው ብለዋል።