ጎርፍን ከስጋት ወደ በረከት መለወጥ እንደሚቻል ተገለፀ
ጥቅምት 03/2018ዓ.ም (ውኢሚ) በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ ላይ በባለፉት ሁለት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች ጎርፍን ከስጋት ወደ በረከት መለወጥ የተቻለ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስተር ክቡር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በአፋርክልል በአሚበራና ዱለቻ ወረዳ ባደረጎት የሥራ ይፋዊ ጉብኝት በባለፉት ሁለት ዓመታት በአዋሽ ወንዝ ላይ በተሰሩ የ255 ኪሎ ሜትር የጎርፍ መከላከያና የወንዝ አመራር ስራዎች ጎርፍን ከስጋት ወደ በረከት መለወጥ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡
ክቡር ሚኒስቴሩ በመስክ ምልከታው እንደገለፁት ቀደም ሲል በጎርፍ አደጋ ምክኒያት ምርት የማይገኝባቸው የእርሻ ቦታዎች ዛሬ ምርት በመስጠት አመርቂ ውጤት ማገኘት ጀምሯል ብለዋል፡፡
አክለውም ክቡር ሚኒስቴሩ ወደ አከባቢው ባለሀብቶች በመግባት የኢንዱስትሪ ጥሪ ግብዓቶችን በማምረት ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል ፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በመስክ ምልከታቸው ይህ ውጤት የመጣው በክረምት ወቅት የሚከሰተውን ጎርፍ በአግባቡ በመያዝ ለምርት ማዋል በመቻሉ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡
በመጨረሻም አሁን በሰራነው የአጭር ጊዜ ስራዎች የተገኘው ውጤት ጎርፍን ከስጋት ወደ በረከት መለወጥ ከተቻለ ወደ ፊት በረጅም ጊዜ የሚሰራ በጥናት ላይ የተመሰረተ ሰፊ ስራዎች በበለጠ ጎርፍ ከስጋት ወቶ እድልና በረከት በመሆን ማህበረሰባችንን የበለጠ ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡
ሥራዊ ጉብኝቱ ነገም የሚቀጥል እንደሚሆን ተገልፆል፡፡