8 ሚሊዬን ብር የሚያወጣ የየቤተሙከራ ልቀት መጠን መለኪያና መቆጣጠሪያ ማሽን/Laboratory Emission Monitoring System/LEMS/ ርክክብ ተደረገ።

8 ሚሊዬን ብር የሚያወጣ የየቤተሙከራ ልቀት መጠን መለኪያና መቆጣጠሪያ ማሽን/Laboratory Emission Monitoring System/LEMS/ ርክክብ ተደረገ። መጋቢት 11/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኤስ ኤን ቪ ኢትዮጵያ /SNV Ethiopia/ 8 ሚሊዬ ብር የሚያወጣ የቤተሙከራ ልቀት መጠን መለኪያና መቆጣጠሪያ ማሽን /Laboratory Emission Monitoring System /LEMS/በይፋ የርክክብ ስነስርዓት ተደርጓል። በመርሃ ግብሩ የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ ወልዱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኢነርጂ ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀው፤ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በስራ ላይ በሚውል የቤተሙከራ የልቀት መጠን መለኪያና መቆጣጠሪያ ማሽን /Laboratory Emission Monitoring System /LEMS/ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢነርጂ ላቦራቶሪ ውስጥ ለትግበራ መብቃቱ ቀጣይነት ያለውን ንፁህ የማብሰያ ቴክኖሎጂ መፍተሄ የሚያመጣ ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ 85 በመቶ የሚሆነው አባወራ ምግብ ለማብሰል በባህላዊ መንገድ ማገዶ /ባዮማስ/ ተጠቃሚ በመሆኑ በተበከለ አየርና ጭስ ምክንያት በተለይ ሴቶችና ህፃናት ለፍተኛ የጤና ችግር እነደሚዳረጉ የገለፁት ስራ አስፈጻሚው ደረጃውን ያልጠበቀ ስቶቭና ማብሰያ ዕቃዎችን በመጠቀም የሀይል ብክነትና የአየር ብክለት በመፈጠሩ ችግሩን ውስብስብ ያደርገዋል ብለዋል። ዛሬ በይፋ የተረከብነው የልቀት መጠን መቆጣጠሪና መለኪያ / Laboratory Emission Monitoring System /LEMS/ የንፁህ ማብሰያ ቴክኖሎጂ ደረጃ አሰጣጥ ጋር ያሉብንን ችግሮች የሚፈታና ንፁህና ደረጃቸውን የጠበቁ ስቶቮችንና የማብሰያ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀምና ለማስተዋወቅ የሚያግዝ ገልጸው፤ ለስኬቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉትን ኤስ ኤን ቪ ኢትዮጵያን/SNV Ethiopia/ እና አጋር ድርጅቶችን አመስግነዋል። ወ/ሮ የትናየት ግርማው የኤስ ኤን ቪ ኢትዮጵያ /SNV Ethiopia/ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሀገራችን አብዛኛው ህብረተሰብ ለምግብ ማብሰያነት ባዮማስ /ማገዶ/ ተጠቃሚ በመሆኑ፤ በተለይ ሴቶችንና ህፃናትን ለከፍተኛ የጤና ችግር የሚዳርግ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተሯ ችግሩን ለመቀነስ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ዛሬ ስራ ላይ እንዲውል በማስረከባቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ ለስኬቱ ምቹ ሁኔታ የፈጠሩትን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችንና ባለሙያዎችን ከልብ አመሰግናለሁ ብለዋል። በመርሃ ግብሩ ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ የሚያደርጉ ቴክኒሻኖች ስልጠና እንደወሰዱ ተገልፆ ለሰልጣኞቹ የምስክር ወረቀት ተበርክቷል። በመድረኩ የባለድርሻ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተወካዮች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅት ተወካዮችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

Share this Post