544 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የቡታጅራ ከተማ የፍሳሽ የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ።

544 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የቡታጅራ ከተማ የፍሳሽ የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ። ሚያዚያ 28/2017 ዓ/ም 544 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የቡታጅራ ከተማ የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የቡታጅራ ከተማ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል። ፕሮጀክቱ ፅዱና ዘመናዊ ከተማን ከመፍጠር ባሻገር ለጤና ጠንቅ የሆኑ የውሃ ወለድ ችግሮችን ይቀርፋል ተብሏል። ፕሮጀክቱ ለወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር በተጨማሪ ለአካባቢ ጥበቃ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል። የሳኒቴሽን ፕሮጀክቱ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አማካኝት ከጣሊያ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚተገበር ነው፡፡

Share this Post