128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተከበረ፡፡

128ኛው የዓድዋ ድል በዓል ተከበረ፡፡

የካቲት 26 /2016 ዓ/ም 128ኛው የዓድዋ ድል “የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ተከበረ።

የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት፤ የኢትዮጵያ ህዝቦች በአንድ ጥሪ ተሰባስበው የኢትዮጵያን ወራሪ ኃይል ድል ማድረጋቸው የህዝባችንን አንድነትና በጋራ ጥቅሞቻችን ላይ መተባበርን እንደሚያመለክት አምባሳደሩ ገልፀዋል።

ህዝብን ይህንን ሲያደርግ በራሱ መሳሪያ እና ስንቅ ከኢትዮጵያ የተሻገረ የጥቁር ሕዝቦች ታሪክ መስራት መቻሉን አምባሳደሩ ገልጸዋል።

የመላ ኢትዮጵያ እና አፍሪካ ተምሳሌት የሆነውን ታሪክ ማሳደግ፣ መዘከር እና ታሪኩን ጠብቆ ለትውልድ ማሸጋገር ይጠበቅብናል ብለዋል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ጌጡ በዓሉን አስመልክቶ ገልፃ ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያከበረ እና ሀገራችን ለማንም እጅ የማትሰጥ መሆኗ ተዳሷል።

በቀረበው ገለፃ ላይ በሰራተኞች ጥያቄ እና አስተያየት የተሰጠ ሲሆን፤ ይህን አኩሪ ታሪክ ያለን ህዝቦች ዛሬ በሰላም እና በልማት መድገም እንደሚገባ ተገጿል።

Share this Post