የኢትዮጵያን የገጠር ኤሌክትሪክ ተዳራሽነት እና አነስተኛ የፀሐይ ብርሃን የኤሌክትሪክ መረቦች ልማት ለማፋጠን የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ሰነዶች ላይ የማረጋገጫ (Validation) ውይይት ተካሄደ።`
የኢትዮጵያን የገጠር ኤሌክትሪክ ተዳራሽነት እና አነስተኛ የፀሐይ ብርሃን የኤሌክትሪክ መረቦች ልማት ለማፋጠን የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ሰነዶች ላይ የማረጋገጫ (Validation) ውይይት ተካሄደ።`
አዲስ አበባ ሐምሌ2 4/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውይይቱ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የኢትዮጵያን የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን አጀንዳ በዘላቂ ሚኒ-ግሪድ ልማት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ሦስት ስትራቴጂያዊ ሰነዶችን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል ።
በዚህም የታዳሽ ኃይል ኢንቨስትመንት ስጋት ቅነሳ (DREI) ትንተና ለሶላር ፎቶቮልታይክ ሚኒ-ግሪዶች፣ የሚኒ-ግሪድ አቅርቦት ሞዴሎችና የተግባር እቅዳቸው፣ የቴክኒክ መመሪያዎችና የብሔራዊ ግሪድ መድረስ ደንቦች፣ እንዲሁም የሚኒ-ግሪድ ንብረቶች የአገልግሎት መጨረሻ ስትራቴጂ እና የቆሻሻ አያያዝ መመሪያዎችን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሰነዶች ናቸውም ብለዋል።
ሰነዶች በመንግስት ተቋማት፣ በልማት አጋሮች፣ በግሉ ዘርፍ፣ በአካዳሚያ እና በአካባቢ ማህበረሰቦች መካከል በተደረገ ሰፊ ምክክር ቴክኒካዊ ትንተና እና ትብብር መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል ።
ኢትዮጵያ የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ግቦቿን እያሳካች በመሄድ ላይ ሳለች በታዳሽ ኃይል የተመሠረቱ ሚኒ-ግሪዶች ከብሔራዊ ግሪድ ውጭ ለሚገኙ ማህበረሰቦች ተመጣጣኝ ተዓማኒ እና ንጹህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ ወሳኝ መፍትሄ መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል ።
በመጨረሻም የኢኮኖሚ ዕድገትን፣ ትምህርትን፣ ጤናን፣ ግብርናን እና የሥራ እድል ፈጠራን የሚያበረታቱ መሆናቸውን ጠቁመው የሚኒ-ግሪዶች ዘላቂ ስኬት ግልጽ ፖሊሲዎች የቁጥጥር ማዕቀፎች፣ ጠንካራ ቴክኒካዊ መስፈርቶች እና ለአካባቢ ተስማሚ አሠራሮች መኖርን የሚጠይቅ ሲሆን ለባለሀብቶች ማህበረሰቦች አስተማማኝ አገልግሎትን ከመንግስት ተቋማት ለቁጥጥር እና ለክትትል ግልጽ መመሪያዎችን የሚፈልጉ በመሆኑ ሚ/ር መስሪያ ቤቱ በዚህ ላይ እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ሰነዶቹ በተለያዩ አካላት የቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎችም በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሀሳብ አስተያየቶች የሰጡና ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቷል።
በመድረኩ ላይ የልማት አጋሮች፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቶች፣ የግል ተቋማት እና የሲቪል ማኅበራት ተወካዮች የተሳትፈዋል።