የብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም (One WASH National Programme - OWNP) ባለፉት ስድስት ዓመታት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ።
የብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም (One WASH National Programme - OWNP) ባለፉት ስድስት ዓመታት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጸ።
ግንቦት15/2018ዓም (ው.ኢ.ሚ) የብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም (One WASH National Programme - OWNP) ባለፉት ስድስት ዓመታት (በተለይም የሁለተኛውን ምዕራፍ ትግበራ አጠናቆ ወደ ሦስተኛው ምዕራፍ እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት) በሀገሪቱ የውሃ፣ ሳኒቴሽንና ሃይጅን (WASH) አቅርቦትን ለማሻሻል ሰፊና የተቀናጁ ሥራዎችን ማከናወኑ ተገለጸ።
የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ አራት ቁልፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ውሃና ኢነርጂ፣ ጤና፣ ትምህርት እና ገንዘብ ሚኒስቴር እንዲሁም የልማት አጋሮችን በማስተባበር በርካታ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል።
ባለፉት ስድስት ዓመታት የተመዘገቡ ዋና ዋና ሥራዎችና ውጤቶች በንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት በገጠር፣ በከተማና በአርብቶ አደር አካባቢዎች የንጹሕ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ የተከናወኑት መጠነ-ሰፊ ሥራዎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድገዋል፤
በዚህም የተቀናጀ ጥረት የንጹሕ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት በከተሞች እንዲሁም በገጠር ላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን በተጠናቀቁትና በመጠናቀቅ ላይ ባሉት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች አዲስ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል።
በሳኒቴሽንና ሃይጅን (የንጽሕና አጠባበቅ) ሥራዎች የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅና በየአካባቢው ያለውን የሳኒቴሽን ችግር ለመቅረፍ በርካታ የግንዛቤ መፍጠሪያና የመሠረተ-ልማት ሥራዎች ተከናውነዋል፤
የፕሮግራሙ አስተባባሪ በማስቀጠል በትምህርት ቤቶችና ጤና ተቋማት የተሰሩ የዋሽ (WASH) መሰረት ልማቶች በተለይ ተጋላጭ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችና ተቋማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ቤት መቅረት (Dropout rate) በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን ገልጸዋል።
በጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶች በመቶዎች በሚቆጠሩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የጤና ኬላዎች፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎችና ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ የውሃና የሽንት ቤት መሠረተ-ልማቶች ተገንብተዋል ለአገልግሎት መብቃታቸውን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ባለፉት ስድስት ዓመታት አመርቂ ውጤቶች ቢመዘገቡም፣ በግምገማ መድረኮች ላይ የተነሱና ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ተግዳሮቶችም ማለትም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ፣የፍሳሽ አወጋገድ ክፍተት፣የክትትልና ጥገና ውስንነትየነበሩ ሲሆን በአጠቃላይ የብሔራዊ ዋን ዋሽ ፕሮግራም ባለፉት ስድስት ዓመታት የሁለተኛውን ምዕራፍ እቅድ በውጤታማነት እያጠናቀቀ የሚገኝ ሲሆን፣ የተገኙ ስኬቶችን በማስቀጠልና የታዩ ክፍተቶችን በመሙላት አሁን ላይ ወደ ምዕራፍ ሦስት (Phase III) ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ትግበራ ለመሸጋገር እየተሰራ መሆኑን በሁለተኛ ምእራፍ ሶስተኛ ሩብ አመት ግምገማ ላይ ተናግረዋል።