የብሄራዊ የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን (one wash) ፕሮግራም አፈፃፀም ተገመገመ።

የብሄራዊ የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን (one wash) ፕሮግራም አፈፃፀም ተገመገመ። ሚያዚያ 16/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ.) ብሄራዊ የአንድ ቋት (National One WaSH) የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን ፕሮግራም አፈጻጸም ተገምግሟል። በፕሮግራሙ ላይ የሚመክረው የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በ15ኛው ስብሰባ እስከ አሁን በሀገር ደረጃ የተከናወኑ የብሄራዊ የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን አፈፃፀሞችን ገምግሟል፡፡ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ባለፉት ዓመታት ንፁህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከክልሎች እና ከፌዴራል ዋን ዋሽ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ተጨባጭ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልፀዋል። ክቡር አምባሳደሩ የአገልግሎት መቆራረጥጦች በኃይል አቅርቦትና የጥጋና ማዕከላት ውስንነቶች ምክንያት የሚፈጠሩ በመሆኑ የአገልግሎት አቅርቦትን በዘላቂነት ለመፍታት የሶላር ሚኒ ግሪድ የመገንባት እና የጥገና ወርክሾፖችን የማደረጀት ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሄራዊ የአንድ ቋት አስተባባሪው አቶ አብይ ግርማ በበኩላቸው የመድረኩ አላማ የብሄራዊ የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን ፕሮግራም እቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ቀሪ የፕሮግራሙ ስራዎች በፍጥነት የሚጠናቀቅበት መንገድ ላይ በመወያየት የ2018 ዓ/ም የእቅድ ረቂቅ ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታላሚ ያደረገ ነው ብለዋል። ንፁህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት በሚለዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ተሳተፊዎቹ ገልፀዋል። ቀጣይነትና ዘላቂት ያለው የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና ኃይጅን አገልግሎት አቅርቦትን በከተማና በገጠር የተሳለጠ ለማድረግ ምን እየተሰራ እንደሆነ ከተሳተፊዎች ለተነሡ ጥያቄዎችም ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለፃና ማብራሪያ ሰጥተዋል። በፕሮግራሙ የታቀፉ አብዛኞቹ ክልሎች የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበባቸው ሲሆን ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የፌዴራልና የክልል ሴክተር አመራሮች በቅርበት እንዲከታተሉ፣ የግዥና የኮንትራት አስተዳደር አሰራሮችን ማሻሸል፣ የፕሮጀክት ባለቤቶች፣ የአማካሪና የስራ ተቋራጮች በመደበኛነት እየተገናኙ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች ማከናወን እና ከግል ሴክተሮች ጋር የምክክር መድረኮችን የማመቻቸት የአፈፃፀም አቅጣጫ ፕሮፖዛል በአስተባባሪው ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ በስትሪንግ ኮሚቴው አቅጣጫ ተሰጥቷዋል። በመርሃ ግብሩ የውሃና ኢነርጂ ፣የጤና፣ የትምህርት እና የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች የተለያዩ የልማት አጋር ድርጅቶች በጋራ መክረዋል።

Share this Post