ዲጂታል የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን(IWRM) ለማጠናከር የሚያስችል አዳዲስ ሶፍት ዌር ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

ዲጂታል የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን(IWRM) ለማጠናከር የሚያስችል አዳዲስ ሶፍት ዌር ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

ሰኔ 1/2018 ዓም(ው.ኢ.ሚ) በኢትዮጵያ ዲጂታል የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን (IWRM) ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገርና የዘርፉን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በሚያስችሉ ሲስተሞች ላይ ውይይት ተካሄደ።

መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢታፋ በንግግራቸው የውሃ ሀብት አስተዳደርን በቴክኖሎጂና በዲጂታል መሠረተ-ልማት መደገፍ ወቅታዊና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሀ ሀብት አስተዳደር ትልቁን ድርሻ ሲወጣ የነበረና ስራውን በማገናዘብ ማስተዳደር አስፈላጊ መሆኑን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሀሳብ ሲሰጥበት የነበረ መሆኑን ገልጸዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በማከል መንግስት ህብረተሰቡ ውሃን ለተለያዩ ስራዎች ለመጠቀም ያለው ንቃተ ህሊና በማየት ባስቀመጠው አቅጣጫ ዘመናዊ የሆነ ወተር ኦዲት ሲስተም ያስፈልጋል ይህም የውሀ ሀብታችን ቆጥረን፣ለክተን አውቀን በዘመናዊ መንገድ ለማስተዳደር ይረዳል ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የውሀ ሀብት አስተዳደርን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ሲሰራና ወደ መሬት ሲወርድ የህብረተሰቡን ፍትሀዊ የውሃ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል በማት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአውደ-ጥናቱን ንግግር ያደረጉት የውሃና መሬት ሀብት ማዕከል (WLRC) ዋናት ዳይሬክተር ዶ/ር ጌቴ ዘለቀ ህረተሰቡም ሆነ ባለሀብቱ ውሃ ከመቀጠልም ባለፈ የሚያርጉት ጥንቃቄ አናሳ መሆኑን ጠቁመው ውሃን በጥንቃቄ እንዲይዙት የመመሪያ ስርዓት እና ተቆጣጣሪ አካል ያፈልጋል ለዚህም የውሃ ዋጋን ህብረተሰቡ እንዲያውቅ የቁጥጥር ስርዓት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ጌቴ በማከል አሁን ላይ ተጠናቀው የሚቀርቡ ሲስተሞች ከላይ የገለጽኩትን ችግሮች ለመፍታት ከውሀ ፈቃድ ጋር ያለውን ነገር ለመፍታት የቁጥጥር ስርዓትን በማስፈን የውሃ አካላትን ቆጠራ፣ኢዲት፣የውሃ ፍሰት ሞኒተር የሚያደርግ አፕልኬሽን መስራታውን ገልጸዋል፡፡

የብራይት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆነቱት ዶ/ር ማማሩ አያሌው በበኩላቸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የውሃ መሬት ሀብት ዲዛይን ያደረጉት የብራይት ፕሮጀክት በአግባቡ ዘለቄታ ባለው ሁኔታ ለመጠቀም አሰራር በተለይ ከተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ጋር ተያይዞ ያሉትን ዋና ዋና ችግሮች ትኩረት ከድርጎ የሚሠራ ፕሮጀክት ዲዛይን መደረጉን ገልጸዋል።

ባለፉት ሁለት አመት ተኩል የተለያዩ አፈጻጸሞችኝ እያሥመዘገበ ቆይቷል ያሉት አስተባባሪው በዚህም ውስጥ አራት ዋና ዋና ተግባራት ያሉት ሲሆን በተለይ 2ኛ አላማው የተፋሰስ መረጃ ማዘመንን በተመለከተ ለውሃ ሀብት አስተዳደር በጣም ወሳኝ በሆኑ ነገሮች ላይ የቴክኒካል ገለጻ በማድረግ በዋናነት ሁለት ዋና ዋና ሲስተሞች ማለትም የውሃ ኦዲት እና ወተር ፐርሚት ዲዛይን ተደርገው ወደ ትግበራ የሚገቡ መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህም ከውሃ ኦዲት ጋር ተያይዞ ሀብታችንን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲሁም ፍትሀዊ የሆነ የውሃ ሀብት አጠቃቀምን ለመዘርጋት ታሳቢ ያደረገ ሲሆን አሁን መሬት ላይ ያለው የውሃ አጠቃቀም ወደፊት ደግሞ መሆን ያለበት ተመዝግቦ የሚያዝበት ስርአት ሲሆን በተለይ ቁልፍ መረጃ በመያዝ ሀገራችን ያለውን ውሃ አጠቃቀም ለማዘመን እንዲሁም ለመቆጣጠር የውሀ አስተዳደር ኤሌክትሮኒክ ፈቃድ በተመለከተ ቴክኒካል ገለጻም አድርገዋል።

ፕሮጀክቱ ለቢሮ፣ለተፋሰስ እንዲሁም ለውሀ ሀብት አስተዳደር ሀላፊዎች በተገኙበት ይህንን ሁለት ሲስተም ማስተዋወቅ ስራእንደሚሠራ እና ከዚህ ቡሀላ ከባለድርሻ አካላት የሚገኘውን ሀሳብ ይዘን ሁሉንም በማሻሻል ወደ ትግበራ የሚገባና የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ትግበራን አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምዳልም ብለዋል።

በዕለቱ የቀረቡትን የቴክኒክ ሰነዶች መነሻ በማድረግ በተሳታፊዎች መካከል ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የአይቲ ባለሙያዎች ቡድንም የበኩሉን ዝግጅት አሳይቷል።

የአውደ-ጥናቱን ማጠቃለያ ውይይትና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የውሃና መሬት ሀብት ማዕከል (WLRC) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌቴ ዘለቀ እና የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ በጋራ በመምራት መርሃ-ግብሩን በስኬት አጠናቀዋል።

በአውደ-ጥናቱ ላይ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር (MoWE) እና ከውሃና መሬት ሀብት ማዕከል (WLRC) የተወከሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዘርፉ ምሁራን ተገኝተዋል።

Share this Post