የሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን (HCO) ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
የሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን (HCO) ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።
አዳማ# ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን (HCO) ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።
ፕሮጀክቱ የትምህርትና የአመጋገብ ስርዓት ውጤታማነትን ለማሻሻል እንደሀገር ከአዲስ አበባ ውጪ በሁሉም ክልሎች በተመረጡ 65 ወሰዳዎች የሚተገበር መሆኑ ተገልጿል።
በስልጠናው መርሃግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪና የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የሚኒስትር ድኤታ ተወካይ አቶ ሞቱማ መቃሳ የሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን (HCO)ፕሮጀክት በውሃና ኢነርጂ በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤናና በሴቶችና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤቶች ቅንጅት፣ ትብብርና በጋራ ዕቅድ የሚተገበርና የሚመራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ በዓለም ባንክ የሚደገፍ እንደሆነና የሰው ሀይል ልማትን በማጠናከር፣ የመሠረታዊ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ጥራት፣ ተደራሽነት ና ቀጣይነት ለማሻሻል ዋና ዓላማ አድርጎ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
ስልጠናው በውሃ ጥራትና ደህንነት ዕቅድ ላይ፣ በውሃ አቅርቦትና ጥገናና በውሃ አቅርቦትና አስተዳደር መረጃ ስርዓት ላይ ያተከረ በመሆኑ አሰልጣኞች ምርጥ ተሞክሮና ልምድ ማካፈል፣ ትኩረት ሰጥተው መከታተልና ገንቢ ሀሳብ ማቅረብ እንዳለባቸው ተናግረዋ።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሂውማን ካፒታል ኦፕሬሽን (HCO) ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ዱጉማ ሰልጣኞች ወደ መጡበት አካበቢ ሲመለሱ ከውሃ ኮሚቴዎችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅትና በትብብር በመስራት የውሃ ጥራትና ደህንነት ለመጠበቅና በራስ አቅም የመጠገን ብቃት ለማዳበር ስልጠናው ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል።
ትክክለኛ፣ ወቅታዊና የተደራጀ የውሃ አቅርቦትና አስተዳደር የመረጃ ስርዓት የዕቅድ ዝግጅትን፣ የአገልግሎት ክትትልንና የውሳኔ አሰጣጥን ለማጠናከር ትልቅ ሚና አለውም ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ወረዳዎች በድርቅ የሚጠቁ፣ግጭት የሚከሰትባቸው ፣በልጆች ዕድገት ላይ መቀንጨር የሚታይባቸውና በስደተኛና ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያዎች በመሆኑ ከሰልጣኞችና ከባለድርሻ አካላት ትልቅ ሀላፊነት ይጠበቃል ብለዋል።
ሰልጣኞች ከህብረተሰቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በስልጠናው ያገኙት ግነዛቤ በዕቅዱ መሠረት ተግባራዊ ካደረጉ በትምህርት ውጤታማነት ፣በልጆች ጤናና ሁለንተናዊ ዕዶገት፣በሴቶች ዕለት ተዕለት ኑሮና ማህባራዊ ህወታቸው ላይ ከፍተኛ መሻሻል ይመጣልም ብለዋል።
በስልጠናው የክልልና የወረዳ የፕሮጀክቱ አሰተባባሪዎቸች፣የባለድርሻ ሴክተር ተወካዮችና የሚኒስቴሩ የዘርፉ ሀላፊዎችና ሙያተኞች ተገኝተዋል።