የትምህርትና የጤና ተቋማት የሶላር ኤሌክትርፍኬሽን ሲስተሞችን በጥራትና በዝቅተኛ ወጪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) በባለቤትነት እንዲያስተዳድር የሚያስችል ጥናት ይፋ ሆነ።

የትምህርትና የጤና ተቋማት የሶላር ኤሌክትርፍኬሽን ሲስተሞችን በጥራትና በዝቅተኛ ወጪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) በባለቤትነት እንዲያስተዳድር የሚያስችል ጥናት ይፋ ሆነ።

ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በADELE ፕሮጀክት ስር የተጠናው ይህ ጥናት በጤና፣ በትምህርት እና በሌሎች ማህበራዊ ተቋማት የተተከሉ የሶላር (Standalone Solar PV) ሲስተሞች ዘላቂ ጥገና አጥተው እንዳይበላሹ የሚያስችል መፍትሔ አቅርቧል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአደሌ ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ስብሰባውን የመሩት የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ጥናቱ ሶስት የአሰራር አማራጮችን ያነጻጸረ ሲሆን EEU በባለቤትነት ይዞ በ'Energy-as-a-Service (EaaS)' ሞዴል የሚያስተዳድርበት ሞዴል በላቀ ሁኔታ መመረጡን ገልጸዋል፡፡

ሞዴሉ የተመረጠበት ምክኒያት ያለው የሰው ሃይል በማጠናር ተቋማቱ በቅርብ ተመከታተል የሚያስችል መዋቅር ያለውና የአገራችን የግል ሴክተር ያላደገ ከመሆኑ አንጻር ይህ ሞዴል ለጤናና ለትምርትተቋማት ቀጣይነት ባለው ሁኔታ አገልግሎት የሚያገኙበት መሆኑ ታሳቢ በማድረግ ነውም ብለዋል።

የተረጋገጠ ዘላቂነት የቀደሙት ልምዶች እንደሚያሳዩት 54% የሚሆኑት ሲስተሞች በባትሪና ኢንቨርተር ብልሽትእንደሚቆሙ የተገለጸ ሲሆን በዚህም EEU ነባር የጥሪ ማዕከሉን (Call Centre)፣ የመለዋወጫ ዕቃዎችን እና የቴክኒሺያን መዋቅሩን በመጠቀም የጥገና ጥራቱን የሚያተኛክር ስራ እንደሚሰራ ተገልጿል ።

የትግበራ ደረጃዎች (Roadmap) በተመለከተ ከውኃና ኢነርጂ፣ ጤና እና ትምህርት ሚኒስቴሮች እንዲሁም ከክልሎች ጋር ስምምነት በመፍጠር ከኮንትራክተሮች ጋር በመስራት የEEU ሰራተኞችን ማሰልጠን እና ከ1,400 በላይ ሲስተሞች መረጃ መሰብሰብ EEU ሙሉ በሙሉ የጥገና እና አስተዳደር ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ከመድረክ ተመላክቷል።

አንድ ወጥ የሆነ ከግሪድ ውጪ የታሪፍ መመሪያ ማጽደቅ እና አሰራሩን ዘላቂ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል።

Share this Post