በማህበረሰብ አቀፍ የውሃ ጥራት ክትትል ስራ (Citizen Science) ፅንሰ ሀሳብ ላይ ተግባር ተኮር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

በማህበረሰብ አቀፍ የውሃ ጥራት ክትትል ስራ (Citizen Science) ፅንሰ ሀሳብ ላይ ተግባር ተኮር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ ሀዋሳ፣ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ Fresh Water Watch ጋር በመተባበር ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች በማህበረሰብ አቀፍ የውሃ ጥራት ክትትል ስራ (Citizen Science) ፅንሰ ሀሳብ ላይ ተግባር ተኮር ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ የስልጠናውን መርሀ ግብር ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ ሳይንስን የሚደግፉ ፍቃደኛ ዜጎችን በማስተባበር የውሃችንን ጤንነት ለመጠበቅ የሚያስችል የአሰራር ስርዓት በመሆኑ ፍቃደኛ ወጣቶችን በማሰልጠን ወደ ስራ ለማስገባት ታሳቢ ያደረገ ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል። Citizen science በተለምዶ ስንጠቀምበት የነበረ ቢሆንም ሳይንሳዊና የዘመኑን ቴክኖሎጂ ታሳቢ ያደረገ የውሃ ጥራት ክትትል ስራ ለመስራት ፍቃደኛ ወጣቶችን (Citizen sciences) ማብቃት የመጀመሪያ ተግባር ነው ያሉት አቶ ደበበ ማህበረሰብ አቀፍ የውሃ ጥራት ክትትል ስራውን ተግባራዊ ለማድረግ በኢትዮጵያን ያሉትን ተፋሰሶች ማዳረስ ባይቻልም በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ቤዚን የሚገኘውን ተሞክሮ ወደሌላው ቤዚን ለማስፋት ያስችላል ብለዋል። በመድረኩ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከአባይ ቤዚን፣ ከአዋሽ ቤዚንና ከስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ቤዚን አስተዳደር ፅ/ቤት የኢኮሀይድሮሎጂና የውሃ ጥራት ቁጥጥር ባለሙያዎች፣ የውሃ ከፍታ አንባቢዎችና እና በሀዋሳ ሀይቆች ዙሪያ ያሉ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይቀጥላል።

Share this Post