የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከCIFF ጋር በንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የሚደረገውን ትብብር አጠናከረ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከCIFF ጋር በንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የሚደረገውን ትብብር አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 21/ 2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው የChildren’s Investment Fund Foundation (CIFF) መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ sir Chris Horn እና የልዑካን ቡድናቸውን በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል ተቀብለው በሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ላይ በስፋት ተወያይተዋል።
ሚኒስቴሩ በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በተሟላ ሁኔታ ለመፈጸም ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት፣ ከሁለትዮሽና ከአጋር ድርጅቶች እንዲሁም ከበጎ አድራጎትና ፋውንዴሽን ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
ከሚኒስቴሩ ጋር በተለይም በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን (WASH) ዘርፍ በትብብር እየሰሩ ካሉ አጋር ተቋማት መካከል CIFF አንዱ ሲሆን፣ ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ የWASH ፕሮግራሞችን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የሚገኘውን ድጋፍ እያጠናከረ እንደሚገኝ በመድረኩ ተጠቅሷል ።
በውይይቱ ወቅት በሚኒስቴሩ በኩል በንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ዘርፍ ለረጅም ጊዜ የቆዩ መሠረታዊ ተግዳሮቶችን፣ አሁን እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና የመንግሥት ፕሮግራሞችን እና በቀጣይ በጋራ ሊሰራባቸው የሚገቡ የትብብር መስኮች ተብራርተዋል።
በተለይም ኢትዮጵያ የሁሉንም ዜጎች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፍላጎትን ለማሟላት የምታደርገውን ጥረት ለማፋጠን በአጋር ተቋማት ሊደረግ የሚችለውን ድጋፍ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የCIFF መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ sir Chris Horn
በበኩላቸው በኢትዮጵያ በንጹህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችንና የታዩ እድገቶችን አድንቀዋል። በተጨማሪም CIFF በመንግሥት ቅድሚያ የሚሰጣቸው አጀንዳዎችን በመከተል ዘርፉን ለመደገፍና ከሚኒስቴሩ ጋር ያለውን ትብብር ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
CIFF ባለፉት ዓመታት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር በመስራት የኢትዮጵያን የWASH ፕሮግራሞች ለማጠናከር የሚደረገውን ጥረት ሲደግፍ የቆየ ሲሆን በዕለቱ በተካሄደው ውይይትም ይህንን ትብብር በቀጣይ ለማጠናከር በሚቻልባቸው የጋራ የሥራ መስኮች ላይም ተጨማሪ ሀሳብ ተለዋውጧል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikt