በዋቢሸበሌ ቤዝን የሚተገበረው የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት (BaSRINET) ማስጀመሪያ መርሃግብር በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
ሚያዚያ 07/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በዋቢሸበሌ ቤዝን የሚተገበረው የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት (Basin Scale Resilience Initiative for Ethiopia/BaSRINET) ማስጀመሪያ መርሃግብር በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው።
መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የየውሃና አነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒሰትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ ፕሮጀክቱ በብሔራዊ የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር ፕሮግራም ከታቀፉ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዋናነት በዋቢ ሸበሌ ቤዚን የአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ማህበረሰቦችን በሚደግፍ መልኩ እንደሚተገበር ጠቁመዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በማከል ፕሮጀክቱ የውሃ ሀብት ጥበቃ፣ በመረጃ ስርዓት ዝርጋታ፣ በውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት እንዲሁም አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ የተቀረጸ መሆኑን አንስተው፤ ፕሮጀክቱ በቤዚኑ የሚገኘውን ውሃ፤ በተለይ በጎርፍ መልክ የሚወጣውን ውሃ በመያዝና ከኢነርጂ አቅርቦት ጋር በማያያዝ ውሃን ለማህበራዊ አገልግሎት ማለትም ለመስኖና መጠጥ አግልግሎት በቀጥታና ዘላቂ በሆነ አግባብ እንዲውሉ በማድረግ የአየርን ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛን ጨምሮ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊን ጨምሮ የሶማሌ ክልል መንግስት ተወካዮች፤ ከኦሮሚያ ክልል የሚመለከታቸው አካላትና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት ይገኛል።
ፕሮጀክቱ በአውሮፓ ህብረትና በጣሊያን መንግሰት የሚደገፍ ነው።