የዓለም ባንክ ከአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ (AUDA–NEPAD) ጋር በመሆን በምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ለሚገኙ የውኃ እና ፋይናንስ ሚንስትሮች ጋር ተወያዩ።

የዓለም ባንክ ከአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ (AUDA–NEPAD) ጋር በመሆን በምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት ለሚገኙ የውኃ እና ፋይናንስ ሚንስትሮች ጋር ተወያዩ።   የዓለም ባንክ ከአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ ጋር ባንኩ በቀጣይ ዓመታት በዘርፉ ከሀገራቱ ጋር ስለሚኖረው የአሰራር ሥርዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል የጋራ መድረክ አካሄደዋል፡፡   የካቲት 8/2018 ዓም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በመደረኩ ላይ ተገኝተው ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት በዘርፉ ልታከናውናቸው በያዘቻቸው ፕሮግራሞች ዙሪያ ጽሑፍ አቅርበዋል፡፡   ክቡር ሚንስትሩ በመድረኩ ለተሳታፊዎቹ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮ ላይ በማተኮር የምትሰራ ሲሆን እነዚሁም የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ተደራሽነትን ማሳደግ፤ መሰረታዊ የሥርዓት ለውጥ ማድረግ እና ለዘርፉ በሚያስፈልገው የመዋዕለ ንዋይ ላይ በልዩ ትኩረት መንቀሳቀስን ያካተተ ነው ብለዋል፡፡   ክቡር ሚንስትሩ አክለውም እነዚህን ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ለማስፈጸም የሚያስችሉ አምዶች የተዘጋጁ ሲሆን በዝርዝር የፕሮግራም ሰነዱ ውስጥ መካተታቸውን ለጉባኤው አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከባንኩ ጋር ለሚኖራት የትብበር ማዕቀፍ ማስፈጸሚያ እንዲሆናት የረጅም ጊዜ ፕሮግራም ሰነድ ማዘጋጀቷንም ገልጸዋል።   በመድረኩ ላይ የገንዘብ ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ሰመሪታ ሰዋሰው፣ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ እና ሌሎች የሚንስቴር መ/ቤቱ አመራረሮች ተገኝተዋል፡፡

Share this Post