የኢነርጂ ዘርፍ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና በመጣው ለውጥ ውይይት ተደረገ ።

የኢነርጂ ዘርፍ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና በመጣው ለውጥ ውይይት ተደረገ ። ሚያዝያ 14/2018 ዓ/ም ውኢሚ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና በመጣው ለውጥ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘርፉ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል። የውይይት መድረኩን ሲመሩ የነበሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ በኢነርጂው ዘርፍ የሚመሩና የሚተገበሩ በርካታ ፕሮጀክቶች እንዳሉ አውስተው በአጠቃላይ ባለፉት 9 ወራትም ይሁን በ5ቱ ዓመታት ጉዞ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። ከሀይል ቆጣቢና ንጹህ የማብሰያ ዕቃዎች አቅርቦት፣ ስርጭትና ተደራሽ ከማድረግ አንፃር 1.2 ሚሊየን ከነበረበት ወደ 2 ሚሊየን መድረሱን ገልፀዋል ። ከሀይል አቅርቦት በ5ቱ ዓመታት ጉዞ ከ4.8 ጊጋ ዋት ወደ 9.7 ጊጋ ዋት ማደጉን ተናግረዋል ። ከሀይል አቅርቦት ጥራት አኳያ የሀይል መቆራረጥ ድግግሞሽና የድግግሞሹ ቆይታ ጊዜ ስሰላ ከፍተኛ መሻሻል መታየቱን ገልፀዋል። ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው ለሚገኙና ገጠራማ አካባቢ ለሚኖሩ ዜጎች በሁሉም ክልል ከ5 እስከ 50 ዋት የሚየመነጭ የፀሐይ ሀይል ማመኔጫ ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል። ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር በግብርናው ዘርፍ የገፀ ምድርንና የከርሰምድርን ውሃ በፀሐይ ሀይል ዘመናዊ ፓምፕ በመጠቀም የመስኖ እርሻን በመስፋት በማምረት የተሻለ ውጤት መታየቱን ተናግረዋል። ዶ/ር ሱልጣን እንደተናገሩት ለኢትዮጵያ የፀሐይ ሀይል ተመራጭ የሚሆነው በምድር ወገብ ላይ በመሆኗ ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል የማግኘት ዕድል ስላላትና የሚመነጨው ሀይል የአየር ብክለት ስለማያስከትልም ነው ብለዋል። ቴክኖሎጂው እየተሻሻለ በመምጣቱ ከአንድ ፓኔል የሚመነጨው ሀይ ሲጨምር የሚወጣው ወጪ እየቀነሰ መምጣቱም ተመራጭ ያደርገዋል ብለዋል። የፀሐይ ሀይል ባለፉት 5 ዓመታት በት/ቤቶች፣በጤና ተቋማት ፣ለሆቴሎችና ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፣በከተሞች አካባቢ ለብረት ስራ፣ለእንጨት ስራ ለፀጉር ቤቶችና ለበረካታ ዘርፈብዙ ለሆኑ ጉዳዮች የሀይል ምንጭ በመሆን የዜጎች ኑሮ እንዲሻሻል አግዟል ብለዋል ። በመጨረሻም ዶ/ር ሱልጣን ከነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚመጡ ዘርፈብዙና ውስብስብ ችግሮችን ለመቋቋም የፀሐይ ሀይል አቅርቦትን ማስፋት አይነተኛ መፍትሄ በመሆኑ በቀጣይ በበለጠ ሁኔታ በመስራት የሻለ ውጤት ማሳየት አለብን ብለዋል። በቀረቡ ሪፖርቶችና ሰነዶች ላይ ውይይት ተደርጓል፣የወደፊት አቅጣጫም ተቀምጧል።

Share this Post