የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ንቅናቄ አሻራቸውን ለማኖር ተዘጋጅተዋል

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ንቅናቄ አሻራቸውን ለማኖር ተዘጋጅተዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አንድ አካል በሆነው በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ንቅናቄ አሻራቸውን ለማኖር ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ለመሥራት መላው ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በዚህም መሰረት ‘ተስፋን እንትከል’ በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ንቅናቄ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ሀብታሙ ኢተፋን (ዶ/ር ኢ/ር) ጨምሮ የሚኒስቴሩና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ይሳተፋሉ።

በዚህም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ወዴቻ ቀበሌ በሚካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በንቃት በመሳተፍ አሻራቸውን ለማኖር ዝግጁ ሆነዋል።

የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ንቅናቄ በመጪው ሰኞ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።

Share this Post