ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ግንባታ የማማከር ውል ስምምነት ተደረገ፡፡

ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ግንባታ የማማከር ውል ስምምነት ተደረገ፡፡ ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን የምስራቅ በለሳ ወረዳ ለቡርሳ የገጠር መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፕሮጀክት የማማከር ስራ ለማከናወን ከላልይበላ ጥናት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር በ 7,264,188 ሚሊየን ብር የውል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ የአካባቢውን ህብረተሰብ ከውሃ ጋር ተያይዞ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በሚመልስ መልኩ ለመፍታትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ጥራቱን ጠብቆ እንዲገነባ የማማከር ስራውን በሚገባ በማከናወን ሀላፊነትን መወጣት እንደሚገባ አሳስበዋል። ተቋሙም የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያርግ ገልፀዋል፡፡ የላልይበላ ጥናት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ፍሰሃ ወንድይፍራው ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው ጊዜ ቀድመው እንደሚያከናውኑ ቃል ገብተዋል፡፡

Share this Post