የኢትዮጵያ የጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ
የኢትዮጵያ የጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ስትሪም ኮሚቴ 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ተካሄደ
ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም. (ው.ሚ.ኢ) – የኢትዮጵያ የጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ስትሪም ኮሚቴ 6ኛ መደበኛ ስብሰባ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተካሄደ።
ስብሰባው የ2018 በጀት ዓመት የፕሮጀክቱን የሥራ አፈጻጸም በመገምገም የተገኙ ውጤቶችን መዳሰስ እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ማጽደቅን ዓላማ አድርጎ ተካሂዷል።
በመድረኩ የ2018 ዓ.ም. አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ቀርቦ በስትሪም ኮሚቴ አባላት ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ፕሮጀክቱ የጎርፍ አደጋን በመቀነስ፣ የእርሻ መሬቶችን ወደ ምርት በመመለስ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም. አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም. ዕቅድ በቀረቡ የማሻሻያ ሀሳቦች መሠረት ተጨማሪ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው በማሳሰብ ስብሰባው ተጠናቋል።
በስብሰባው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አመራሮች እና የፋይናንስ ሚኒስቴር ተወካዮች በመገኘት በሪፖርቱና በቀጣይ የሥራ ዕቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል::