የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሁለተኛው የከተሞች ዋሽ ፕሮግራም የተገዙ 44 ሞተሮችን ለ22 ከተሞች አበረከተ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሁለተኛው የከተሞች ዋሽ ፕሮግራም የተገዙ 44 ሞተሮችን ለ22 ከተሞች አበረከተ፡፡ መጋቢት /2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመጠጥ ውሃና ሳንቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ በሁለተኛው የከተሞች ዋሽ ፕሮግራም የተገዙ 44 ሞተር ሳይክሎች ለ22 ከተሞች የውሃ አገልግሎት ተወካዮች አስረክበዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ርክክቡን ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት ሞተሮቹ የከተሞችን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የአቅም ግንባታ አካል ሆነው የተገዙ ናቸው ብለዋል፡፡ ክቡር አምባሳደሩ በማከል ለ22 ከተሞች ሁለት ሁለት ሞተር ሳይክሎች ለከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ክትትልና ድጋፍ እንዲረዳ ታሳቢ በማድረግ የተሰጡ መሆኑን ገልጸው፤ ሞተሮቹ ለፖሮግራሙ ብቻ እንዲጠቀሙባቸው በማሳሰብ ክትትል እንደሚደረግና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉም በጥንቃቄ መያዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ሞተር ሳይክሎቹ በሁለተኛው የከተሞች ዋሽ ፕሮግራም በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተገዙና በሀግቤስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ካምፓኒ በተገባ ውል መሰረት የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

Share this Post