የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ 435 ቤተሰቦች የበዓል መዋያ ድጋፍ ተደረገ።

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ 435 ቤተሰቦች የበዓል መዋያ ድጋፍ ተደረገ። መጋቢት 30/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ለሚገኙ አቅመ ደካሞች እና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ። በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በሰላም ወተን በሰላም በመግባታችን በአመቱ ለመገናኘት ያበቃንን ፈጣሪ በማመስገን በየበአሉ ያለንን ከቤተሰቦቻችን ጋር ስናሳልፍ ትልቅ ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ያለውን ተካፍሎ አብሮ መብላት የኢትዮጵያውያን ከሌላው አለም የሚለየን ትርጉም ያለው የቆየ ባህላችን በመሆኑ እስካለን ድረስ የምናስቀጥለው ይሆናል ብለዋል። በመሆኑም እኛ ካለን ላይ ስናካፍል እናንተም በአካባቢያችሁ እድሉን ያላገኙ ቤተሰቦቻችሁን በማሰብ አንዱ ለአንዱ የመድረስ ባህላችንን አጠናክረን መቀጠል ይገባል በማለት አሳስበዋል። በዕለቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞች፣ ከቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 እና ወረዳ 6 ለተውጣጡ አቅመ ደካሞች በአጠቃላይ ለ435 ሰዎች ከ3.6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ለበዓል መዋያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። ድጋፍ የተደረገላቸው ቤተሰቦችም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በየበአሉ ለሚያደርግላቸው ድጋፍ ሁሉ አመስግነዋል።

Share this Post