ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ ጥናት፣ ዲዛይንና ኤሌክትሮ መካናኒክ እቃዎች አቅርቦት ውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ ጥናት፣ዲዛይንና ኤሌክትሮ መካናኒክ እቃዎች አቅርቦት ውል ስምምነት ተፈረመ።   መጋቢት 9/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ፣ በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎች ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ፣ ጥናት፣ ዲዛይንና ኤሌክትሮ መካናኒክ እቃዎች አቅርቦት ከስምንት ድርጂቶች ጋር ውል ስምምነት ተፈራረመ።   ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል። ፕሮጀክቶቹ በአራት ክልሎች እንደሚተገበሩ የገለጹት ክብር አምባሳደሩ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ከመንግስት በተያዘ በጀት ስራው እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡   ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው አካባቢዎች በአማራ ክልል መካነ ሰላም፣ሰቆጣ እና ገለሱት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ጀልዱ ወረዳ ጎጆ ከተማ፣ በትግራይ ክልል ማይጸብሪ፣ በጋምቤላ ክልል ሲሆኑ ድርቅ የሚያጠቃቸው አካባቢዎች በመሆናቸው ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡   ኮንትራት የወሰዱት አማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን የመካነ ሰላምና ሰቆጣ የመጠጥ ውሃ ግንባታ 253‚573‚787 ብር አግራባት ኮንስትራክሽን የገለሱት መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የኤልክትሮ መካኒክ እቃ አቅርቦት በ80‚954 ብር በላይ ማንቴክ ኢንጂነሪንግ ለማይጸብሪ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የኤሌክትሮ መካኒክ እቃ አቅርቦት በ12‚355‚475 ብር ጎጆ አማካሪ ጀዱ ወረዳ የመጠጥ ውሃ ግንባታ የጥናት በ14 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ናይል ሊቾዌ ጀኔራል ኮንትራክተር በጋምቤላ ክልል ሁለት የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በ20 ሚሊዮን ብር ውል የተገባና ኮንትራክተሮች ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰሩ ያሉ መሆናቸውን ገልጸው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀድመው እንደሚያጠናቅቁ በኢ/ር ሰላማዊት ሰይድ በኩል ቃል ገብተዋል፡፡   የግንባታ ፕሮከጅቶቹ በ6 ወር የጊዜ ገደብ የዕቃ አቅርቦት የአንድ ወር እና ጉድጓድ ቁፋሮ በ3 ወር የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁ ተገልጿል፡፡

Share this Post