ከ331 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የባለብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ331 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የባለብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ። ሰኔ 04/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቡርጂ ዞን ሶያማ ዙሪያ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል እና በCR-WaSH ፕሮጀክት የሚተገበር ባለ ብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ የውል ስምምነት ተፈረመ። ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል። ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም የደቡብ ኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር፣ የክልሉና የዞን አመራሮች ድጋፍ እንዲያደርጉ እና በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ የአክሚ ኢንጂነሪንግና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ኃይሉ ሰይፉ ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብቀድመው እንደሚያጠናቅቁ ቃል ገብተዋል፡፡ ጃርሶ የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ከአክሚ ኢንጂነሪንግና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ጋር የውል ስምምነቱን ወስደዋል። ፕሮጀክቱ በ1 ዓመት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ 16,177 የህብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

Share this Post