ከ294 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ294 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ሰኔ 30/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የዛላ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ከ294 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለማከናወን ከሾዴብ ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. ጋር የግንባታ የውል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የተራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል።

ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም በዋን ዋሽ ናሽናል ሮግራም እንደሚተገበር ገልፀው ፕሮጀክቶቹ የሚተገበሩት ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች በመሆናቸው ግንባታው ከህረተሰቡ በተጨማሪ የቤት እንስሳትንም ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አንስተው፤ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ሾዴብ ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ.ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ተድላ ጫንያለው ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰሩ ያሉና አካቢውን በቅርበት ስለምናውቀው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ አጠናቀው እንደሚያስረክ ቃል ገብተዋል፡፡

በዋን ዋሽ ፕሮግራም በCR-WaSH ፕሮጀክት የሚተገበተው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የቧንቧዎች ፣ የመገጣጠሚያዎች እና የኤሌክትሮ-ሜካኒካል መሳሪያዎች አቅርቦት፣ ዝርጋታንና ግንባታን የሚያካትት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ 9 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡ ፕሮጀክቱ የእንስሳት የውሃ ማቅረቢያ ገንዳ የተካተተበት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Share this Post