የ272, 272.3 የአሜሪካ ዶላር የእቃ አቅርቦትና አገልግሎት የውል ስምምነት ተፈረመ።

የ272, 272.3 የአሜሪካ ዶላር የእቃ አቅርቦትና አገልግሎት የውል ስምምነት ተፈረመ።

መጋቢት 4/2016ዓ.ም የውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር (ው.ኢ.ሚ) ለኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጅ ኢንስቲቲዩት አገልግሎት የሚውል 12 አውቶማቲክ የአየር ንብረት መከታተያ ስቴሽን ( Automatic weather station) አቅርቦት እና 6 የዘርፉ ባለሙያዎችን በመሳሪያው አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል የ272,272.3 ሺ ዶላር የውል ስምምነት ከጀርመኑ OTT Hydromet መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር ተደርጓል።

ስምምነቱን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞና የድርጅቱ ም/ፕሬዘዳንት Mr.Prats Jossellin ተፈራርመዋል።

ስምምነቱም ከ12_14 ሳምንታት ባለው ጊዜ ውስጥ ተፈጻሚ እንደሚሆን በተገባው ውል ተቀምጧል።

Share this Post