ከ224 ሚሊየን 784 ሺ ብር በላይ በሚሆን ወጭ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ224 ሚሊየን 784 ሺ ብር በላይ በሚሆን ወጭ የመጠጥ ውሃ ግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ። መጋቢት 23/5017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ224 ሚሊዮን 784 ሺ ብር በላይ በሚሆን ወጭ የመጠጥ ውሃ ግንባታ የውል ስምምነት ተፈራርማል። በዋን ዋሽ ፕሮግራም የያያ ወርቄ ሲአር ዋሽ ባለብዙ መንደር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የሚገነባ ሲሆን ጀማል አህመድ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የውል ስምምነቱን ወስዷል። የመጠጥ ውሃ ግንባታው በ15 ወራት ተጠናቆ አገልግሎት እንዲሰጥ ውል የተገባ ሲሆን ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ከ13ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ታውቋል። ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃ እና በተቀመጠው ጊዜ ፕሮጀክቱን ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

Share this Post