የምስራቅ አፍሪካ የሀይል ትስስር 22ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በይፋ ተጀምሯል።

የምስራቅ አፍሪካ የሀይል ትስስር 22ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በይፋ ተጀምሯል።

ሐምሌ 2/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የምስራቅ አፍሪካ የሀይል ትስስር 22ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በስካይላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር (Eastern Africa Power Pool) የተመሰረተው ሰፊ ዓላማን አንግቦ ሲሆን የቀጣናውና የጎረቤት ሀገራት ትብብር ስኬታማ የሚሆነው ሀገራት በፈቃዳቸው በጋራ ህጎች በመመራት ሲስማሙ ነው በሚለው መርህ መመራት ሲችሉ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በግብፅ መሪነት ሲካሄድ በነበረው የምስራቅ አፍሪካ የሀይል ትስስር የኤሌክትሪክ ገበያን በተግባር ለማስጀመር እና ተቋማዊ ልማትን ለማስቀጠል ከፍተኛ ጥረቶች ሲደረጉበት እንደቆዩ አውስተው አሁንም ኢትዮጵያ የሰብሳቢነቱን ኃላፊነት ስትረከብ ለተደረጉት ጥረቶች ክብር በመስጠት ከሁሉም አባል ሀገራት ጋር በቅርብ ለመስራት ባለው ቁርጠኝነት የጋራ ራዕያችንን ለማሳካት ጽኑ አቋም አለን ብለዋል።

የዚህ ልዩ ስብሰባ ዓላማ በእጅጉ አስፈላጊ ሲሆን አባል ሀገራቱ በተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶችና ተያያዥ አስተዳደራዊ መመሪያና ደንቦች ላይ የቀረቡትን የማሻሻያ ረቂቆች በተመለከተ አስተያየታቸው የሚቀርብበት ሲሆን የምክረ ሀሳቦቹ ውጤቶች በድጋሚ ታይተው ውጤቶቹ ይፋ የሚሆኑበት ይሆናል።

Share this Post