ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ6ወራት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ።
ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የ6ወራት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ።
ጥር 30/2017ዓ.ም አዲስ አበባ (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2017ዓ.ም የበጀት ዓመት የ6ወራት እቅድ አፈጻጸምን ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ገምግሟል።
በስድስት ወራቱ በየዘርፎቹ የታቀዱ ፣ የተከናወኑ ፣ የነበሩ ጠንካራ ስራዎችና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን የሁሉም ዘርፎች ቁልፍ አፈጻጸምም 93.73 በመቶ መሆኑ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል።
ተግባራትን በመፈጸም ሂደትም ያጋጠሙ ችግሮች በዝርዝር በሪፖርቱ ተካተው ቀርበዋል።
አጠቃላይ መረጃዎችን በጥራት ማደራጀት፣ የፕሮጀክቶችን ክትትልና ድጋፍ ስርዓትን ማጠናከር፣ የጨሬታና ግምገማ ሂደትን ማቀላጠፍ ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የትብብርና ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ፣ የሰው ሀይልን በተገቢው መንገድ በመምራት አጥጋቢ ውጤት ማስመዝገብ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ተደራሽነትን ማስፋት፣ የአማካሪ፣ኮንትራክተርና የፕሮጀክት ባለቤት የጋራ መድረክን ማጠናከር እንዲሁም የሚዘጋጁ የጨረታ ሰነዶችና ዲዛይኖች በሀገር በቀል ምርት የሚስተናገዱበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውም በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል።
በተያያዘ ዜና ለረጅም ጊዜ ሳይሻሻሉ የቆዩና አሁን ላይ በውሃ ሀብቱም ሆነ በኢነርጂ ልማቱ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የተሻሻሉ የኢትዮጵያ የውሃ ፖሊሲና እና የኢነርጂ ፖሊሲ ረቂቆች ለጠቅላላ ሰራተኛው ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በውይይቱም በርካታ ገንቢ ሀሳብች ፣ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተንጸባርቀዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተውበታል።