ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ።
ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገመ።
ሀምሌ 3/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የ2017 ዓ.ም የበጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸምን ከክልል ቤዚን ጽ/ቤቶች፣ ፕሮጀክቶች አስተባባሪዎችእና አጠቃላይ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ገምግሟል።
መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ በ2017 በጀት አመት በየዘርፉ የታቀዱ ፣ የተከናወኑ፣ የነበሩ ጠንካራ ስራዎችና መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ሰራተኛ እንዲሳተፍ መደረጉን ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ በዘርፉ ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ትኩረት ይደረጋልም ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በማከል በዘርፉ ብዙ ፕሮጀክቶች በተበታተነ መልኩ መኖራቸውን ገልጸው፤ ወደ አንድ አምጥተን እንዴት እንሰራለን፤ እንዴት በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ እናደርጋለን፤ ምን ውስጥ ነበርን፤ ምን ውጤት አመጣን፤ በቀጣይ ምን እንሰራለን፤ የሚለውን የሚታይበት ስለሆነ ሁሉም ተሳታፊ በንቃት እንዲሳተፍ አሳስበዋል።
በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ በዘርፉ ስለተከናወኑ ስትራቴጂያዊ ተግባራት በተፋሰስ ዕቅድ ላይ የተመሰረተ የውሃ ሀብት አስተዳዳር ስራዎችን ማከናወን፤ በፈቃድ ምደባና ክፍያ ላይ የተመሰረተ የውሃ አጠቃቀም መተግበር፤ የውሃ ሀብት አስተዳዳር ዝርዝር የህግና የትግበራ ማዕቀፎችን ማዘጋጀትና መተግበር፤ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ትብብር ማጠናከር እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማካሄድ ላይ ጥሩ አፈጻጸም እዳሳዩ ገልጸዋል፡፡
አቶ ደበበ በማያያዝ የክረምት ወራት የአርንጓዴ አሻራና የጎርፍ መከላከል ስራዎችን መከታተልና ውጤታማ ማድረግ፤ የቤዚን ፕላን ዝግጅትንና ትግበራን ፕላት ፎርሞችን ማጠናከር፤ የሰው ሀይል ክፍተትን መሙላትና የአቅም ግንባታ ስራዎችን በስፋት ማከናወን፤ ለውሃ ሀብት አስተዳዳር ወሳኝ የሆኑ የውሃ ፖሊሲ፣ ህግና ማስፈጸሚያ ማዕቀፎች፣ መመሪያዎችን፣ ስታንዳርዶችን ስራ ላይ ማዋል፤ የመደበኛና ፕሮጀክቶች (የአጋር ድርጅቶችን ፕሮጀክቶች ጨምሮ) ማስተሳሰርና ውጤታማ ማድረግ፤ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውም በቀረቡት ሪፖርት አመላክተዋል።
ተግባራትን በመፈጸም ሂደትም ያጋጠሙ ችግሮች በዝርዝር በሪፖርቱ ተካተው የቀረቡ ሲሆን በውይይቱም በርካታ ገንቢ ሀሳብች ፣ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተንጸባርቀዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት በሚኒስትር ዲኤታ ማእረግ ክቡር ሚንስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መልስ ሰጥተውበታል።