የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዘርፎች እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደረገ።
መጋቢት 07/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በ2017 በጀት ዓመት የማክሮ ኢኮኖሚ እና ዘርፎች የ9ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት አደረጉ ።
የማክሮ የኢኮኖሚ እና የዘርፎች የ9ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንደሀገር ኢትዮጵያ ያለችበት ደረጃ ምን ይመስላል፣ ምን አሳክተናል፣ ማሻሻያዎቹስ ምን ለውጥ አመጡ የሚለውን በጋራ ለመገምገም ያለመ መድረክ መሆኑን ጠቁመዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም ሪፖርቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ እና በተለያዩ መስኮች ማለትም አለማቀፍ ኢኮኖሚ አዝማሚያና በኢትዮጵያ ያለው አንድምታ፣ የኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤቶችና አዝማሚያዎች እንዲሁም የዋና ዋና ፕሮጀክቶች አፈፃፀምን የያዘ በመሆኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ያስመዘገብናቸው ስኬቶች፣ የውጭ ምንዛሬያችን ያለበት ደረጃ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና መንገዶች ና የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም የምናይበት ነው ብለዋል።
በውይይቱ ተቋማችን እንደ አስፈፃሚ መስሪያ ቤት ራሳችንን እንድናይ ስለሚያደርገን የምናነሳቸው ጉዳዮች በቀጣይ በምናቅደው ዕቅድ ውስጥ ለማካተትና የጋራ ለማድረግ እንዲያስችል ሁሉም ሰራተኛ ተሳትፎ እንዲያደርግ ክቡር ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ አለሙ መንገሻ የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና የዘርፎች ዕቅድ ሪፓርት እንደ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት ምን አቅደን ምን ያህሉን አሳክተናል፣ ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካች (KPI) ምን ይመስላል ፣የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም ፣የተሠጠ አቅም ግንባታ ድጋፍ እና በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫን በሚያመላክት የቴክኒክና የድጋፍ ሰጪ የስራ ክፍሎችን የ9ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር አብራርተዋል።