የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣የተጠሪ ተቋማትና የክልል ውሀና ኢነርጅ ቢሮዎች የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት እቅድ ለውይይት ቀረበ።
የውሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ፣ የኢነርጅ ልማት እና የመጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፉን በተቀናጀ መልኩ በዘላቂነት በመምራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ዋነኛ አላማው ነው። ለዚህ አላማ መሳካት መግሞ እቅድ ላይ ውይይት ማካሄድ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።
በዚህም መሰረት በባህር ዳር ከተማ ከመስከረም 13/2015ኣ.ም ጀምሮ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ የክልል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮዎች፤ በመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ሳኒቴሽን አገልግሎት፤ የኢነርጅ ልማትንና የዉሃ ሀብት አስተዳደርን አስመልክቶ የ2015 ዓ.ም እቅዳቸውን ለውይይት አቅርበዋል።
መርሃ ግብሩ ቀጥሎ በቀረቡ እቅዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግና ከውይይቱም በርካታ ጠቃሚ ሀሳቦችና ተሞክሮዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።