በ 195 ሚ ብር ወጪ 370 ኪሎ ዋት ማመንጨት የሚችል የሶላር ኃይል ማመንጫ ተመረቀ።

በ 195 ሚ ብር ወጪ 370 ኪሎ ዋት ማመንጨት የሚችል የሶላር ኃይል ማመንጫ ተመረቀ። ታህሳስ 05/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከGIZ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ጋር በመተባበር በ195 ሚ ብር ወጪ ያስገነባውን 370 ኪሎ ዋት ማመንጨት የሚችል የኦዳ ሶላር ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አስመረቀ። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የተመራ ቡድን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን መደወላቡ ወረዳ ኦቦርሶ ቀበሌ በኦዳ ሶላር ሚኒ ግሪድ ሳይት ላይ በተደረገው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልእክት 15 ሺ የገጠሩን ማህበረሰብ ንፁህ ኢነርጂ ተጠቃሚ ለማድረግ ተግባራዊ የሚደረገው ፕሮጀክት ለመብራት፣ ለማብሰያ፣ ለግብርናና ለከተማ ውስጥ አገልግሎት የሚውል ትልቅ ፕሮጀክት በመሆኑ ለአካባቢው ማህበረሰብም የስራ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል። ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም ባለፉት አመታት በኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆኑን ገልፀው ፕሮጀከቱ በገጠርም ሆነ በከተማ የሚከናወነውን የልማት እንቅስቃሴ ይደግፋል፡ እንደ እንጨት ስራና የመሳሰሉትንም በመጠቀም ለአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል የሚፈጥር በመሆኑ የአካባቢው ህብረተሰብ እንደራሱ ንብረት በመጠበቅ የጋራ ሀብት አጠቃቀምን ልምድ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። የኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ሚሊዮን በቀለ በበኩላቸው የአካባቢው ህብረተሰብ ያገኘውን የመብራት አገልግሎት በዘላቂነት ለመጠቀም ማህበረሰቡ እንዲንከባከብና እንዲጠብቅ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ፅ/ቤት አቶ ተሾመ ሞሲሳ ፕሮጀክቱ እንደ ኦሮሚያ ክልል የመብራት ተጠቃሚ ከማድረግ ባሽአገር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ አስተዋፃኦ ያደረጉትን እካላት አመስግነዋል፡፡ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን የቦረና ዞን አስተዳዳሪ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት በከተማና በገጠር ለሚኖሩ ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠሩ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡ በመድረኩ የጂአይዜድ ፕሮግራም ማናጀር Mr Al Mudabbir Bin Anamን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረትና የአለም ባንክ ተወካዮች፣ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች፣ ኮንትራክተርና አማካሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የቀበሌው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post