ከ16ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚደርግ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ16ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚደርግ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ሰኔ 30/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሃመር ወረዳ ከ97 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የዲሜካ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ለማስገንባት ከባይጌታ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ጋር የውል ስምምነት ተፈርሟል።

በCR-WaSH ፕሮጀክት የሚተገበረው የመጠጥ ውሃ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከ16ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን የሲቪል ስራ ግንባታ፣ የቧንቧ ዝርጋታ እና የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ተከላ ስራዎችን አጠቃሎ እንደሚተገበርም በውል ስምምነቱ ተገልጿል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል።

ክቡር አምባሳደሩ ፕሮጀክቶቹ የሚተገበሩት ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች በመሆናቸው ግንባታው ከህረተሰቡ በተጨማሪ ለእንስሳዎችም ጭምር በመሆኑ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ባይጌታ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማ.ስራ አስኪያጅ ተሾመ ታገሰ ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በርካታ ስራዎችን መስራታቸውን ገልጸው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀድመው በማጠናቀቅ እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በ9ወር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ 16 ሺ 361 የህብረተሰብ ክፍሎችንና እንስሳትን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

የማማከር ስራውን የደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ኮንስትራክሽን ቁጥጥር ድርጅት እንደሚሠራውም ማወቅ ተችሏል፡፡

Share this Post