ከ139 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ139 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የውል ስምምነት ተፈረመ።   የካቲት 3/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት አካል የሆኑ 11ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን እንዲሁም የግንባታ ክትትል ለማድረግ በ139 ሚሊየን 191 ሺ 728ብር ከ57 ሳንቲም በሆነ ወጭ የውል ስምምነት ተፈራርሟል።   ስምምነቱን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ከሬድዋን ሀይድሮሎጂ ሶሉሽንስ አማካሪ ድርጅት እና ከአይጄፍ የውሃ ስራዎችና ቢዝነስ አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር ተፈራርመዋል።   የውል ስምምነት የተወሰደባቸው ፕሮጀክቶች 11ሲሆኑ በአፋር ክልል 3፣ በአማራ ክልል 2፣ በኦሮሚያ ክልል 2 እና ድሬዳዋ 4 ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን እና የግንባታ ክትትል ለማከናወን የተደረገ ነው ተብሏል። የማማከር አገልግሎቱ ውል በሚቀጥሉት 12 ወራት የሚጠናቀቅ ሲሆን የፕሮጀክቶቹ ፋይናንስ ሙሉ ለሙሉ በአለም ባንክ ድጋፍ የሚከናወን መሆኑም ተገልጿል።   ፕሮጀክቶቹ አስቸኳይ በመሆናቸው ውል የወሰዱ ድርጅቶች ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብ በጥሩ አፈጻጸም በመተግበር በተቀመጠው ጊዜ ማጠናቀቅ እንደሚገባ ክቡር አቶ ሞቱማ አጽንኦት ሰጥተዋል።

Share this Post