ከ135ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ135ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የግንባታ ውል ስምምነት ተፈረመ።

ሰኔ 30/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበናፀማይ ወረዳ የአልተርጉዴ ቀበሌ ከ135ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችል በCR-WaSH ፕሮጀክት የሚተገበር የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከገነነ ኩማሎ ጠቅላላ የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ጋር የግንባታ የውል ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱ የሲቪል ስራ ግንባታ፣ የእቃ አቅርቦትና የቧንቧ ዝርጋታ ፣ ፊቲንግ ፣ ዲዛይን ግምገማ፣ እና ተከላ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች (ሶላር ሲስተም) የሚያጠቃልል መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል።

ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም በዋንዋሽ ናሽናል ሮግራም በሚተገበረው ፕሮጀክት የሚኖሩት ማህበረሰቦች አርብቶ አደርና ድርቅ የሚያጠቃቸው አካባቢዎች በመሆናቸው ግንባታው ከህብረተሰቡ በተጨማሪ ለእንስሳትም ጭምር በመሆኑ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

የገነነ ኩማሎ ጠቅላላ የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገነነ ኩማሎ ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰሩ ያሉ መሆናቸውን ገልጸው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀድመው እንደሚያጠናቅቁ ቃል ገብተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በ9 ወር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ከ 8 ሽህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ለቤት እንስሳትም ውሃ ለማቅረብ ታሳቢ የተደረገበት ነው።

Share this Post