ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጥናት፣ዲዛይንና ግንባታ ክትትል ውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጥናት፣ዲዛይንና ግንባታ ክትትል ውል ስምምነት ተፈረመ።   የካቲት 26/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ክልል አምስት ወረዳዎች ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጥናት፣ዲዛይንና ግንባታ ክትትል ውል ስምምነት ከላሊበላ የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ። ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ፕሮጀክቱን በማጠናቀቅ የህብረተሰቡ የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ አሳስበዋል።   ክቡር አምባሳደሩ አያይዘውም የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት በአጠቃላይ በ110 የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች በ55 ወረዳዎች እየተገነቡ እና ፕሮጀክቱ በከርሰ ምድር ውሃ ጥናት፣በከርሰ ምድር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም በመስኖ ልማት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡   አሁን ላይ ፕሮጀክቱ የ88 መጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን አማካሪ ቅጥር በማውጣት እስከ አሁን የ65 ፕሮጀክቶች ቅጥር መፈጸሙን ጠቅሰው በዛሬው እለትም ከ120 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጥናት፣ዲዛይንና ግንባታ ክትትል ውል ስምምነት መፈረሚንና አማካሪ ድርጂቱም በ12 ወር የጊዜ ገደብ ባጠረ እንዲያጠናቅቅ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በኩልም የተለመደው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡   ከላሊበላ የጥናት፣ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር ስራ አስኪያጂ ኢ/ር ፍስሀ ወንዲፍራው ከዚህ በፊት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ብዙ ስራዎችን እየሰሩ እና አካባቢውንም የሚያውቁት መሆናቸውን ገልጸው ስራውን በጥራትና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀድመው እንደሚያጠናቅቁ ቃል ገብተዋል፡፡   ፕሮጀክቶቹ በአማራ ክልል ታች አርማጭሆ ወረዳ፣ ምእራብ አርማጭሆ ወረዳ፣ ጭልጋ ወረዳ፣መተማ ወረዳ እና ማእከላዊ ጎንደር የሚተገበሩ ሲሆን ወጪው ሙሉ በሙሉ ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወን ነው፡፡

Share this Post