ከ110 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጭ የውል ስምምነት ተፈረመ፡፡
ሰኔ 5/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ110 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጭ ለኮንስትራክሽን ቁጥጥር፣ የኮንትራት አስተዳደርና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን የውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ልማት ፈንድ የተሻሻለ የንጽህና አጠባበቅ አገልግሎት መስጫ ፕሮጀክት አካል የሆነው ለ6 ከተሞች ለኮንስትራክሽን ቁጥጥር፣ የኮንትራት አስተዳደርና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ለማከናወን SWS እና SRL አማካሪ ከመታፈሪያ አማካሪ ድርጅት ጋር በጋራ ከ110 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጭ የውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የውል ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ SWS እና SRL አማካሪ ከመታፈሪያ አማካሪ ድርጅት ጋር በገቡት ውል መሰረት ለስድስት ከተሞች (አረርቲ፣ እንጅባራ፣ ቡታጅራ፣ ሆሣዕና፣ ቡራዩ እና ፍቼ ) ከተሞች የዝቃጭ ማጣሪያ ግንባታ፣ ያልተማከለ የፍሳሽ ማጣሪያ ሥርዓት እና የሕዝብና የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን በሚፈለገው ደረጃ በጥራትና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተገንብቶ የህብረተሰቡን ችግር እንዲፈታ ታሳቢ ያደረገ የውል ስምምነት ነው ብለዋል፡፡
የውል ስምምነቱን የወሰደው SWS እና SRL አማካሪ ከመታፈሪያ አማካሪ ድርጅት ሚስተር ጂያንአንካርሎ ቺጋሪኒ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ውል የወሰዱ መሆኑን ጠቅሰው በዘርፉ ያላቸውን ልምድ ተጠቅመው በታለመለት ጊዜና ጥራት እንደሚያከናውኑ ቃል ገብተዋል፡፡
የገንዘብ ድጋፉ ከጣሊያን መንግስት የተገኘ ሲሆን በአንድ አመት የጊዜ ገደብ የሚተገር መሆኑም ታውቋል።