እ.ኤ.አ ከሜይ 11 እስከ 20/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ
እ.ኤ.አ ከሜይ 11 እስከ 20/2024 የሚኖረው የአየር ሁኔታ
///////////
በመደበኛ ሁኔታ በሜይ ሁሉተኛው አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ በመጠንም ሆነ በሥርጭት ቀስ በቀስ ከሰሜን ምሥራቅ ላይ እየቀነሰ ወደ ምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እየተስፋፋ ይሄዳል:: በተጨማሪም በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍሎች ላይ ዝናቡ ቀጣይነት ይኖረዋል።
በሜይ ሁለተኛው አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ ሊያደርጉ የሚችሉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በደቡብ አጋማሽ ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሚቀጥሉት አሥር ቀናት የበልግ ዝናብ ተጠቃሚ ስፍራዎች ላይ ለዝናብ መፈጠር አመቺ የሆኑ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ጥንካሬ እንደሚኖራቸውና በተለይም በልግ ዋናኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ፣ በምስራቅ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ።